ሌብነትና ብልሹ አሰራር ቁልፍ ችግር እየሆነ መጥቷል፡፡
ሌብነትና ብልሹ አሰራር ቁልፍ ችግር እየሆነ መጥቷል፡፡
አዲስ አበባ፤ ጥር 19 ቀን 2018 ዓ.ም
የሌብነትና ብልሹ አሰራር ችግሮችን ለመፍታት የቁጥጥርና የተጠያቂነት አሰራር ሥርዓትን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ በአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መርጋ ጢጣ ገልፀዋል፡፡
ከሥራ ክፍላችን ጋር ቆይታ ያደረጉት አቶ መርጋ ጢጣ በ2018 በጀት ዓመት በመጀመሪያው 6 ወራት 3 በአስቸኳይ ጊዜ እና አንድ በመደበኛ በጥቅሉ 4 ጥቆማዎች ቀርበው በመደበኛ ጥቆማ የቀረበው አግባብነት የሌለው ሲሆን በአስቼኳይ ጊዜ ጥቆማ ከቀረቡት ውስጥ አንዱን ችግሩ እንዲፈታ አድርገናል፤ ሁለቱን ደግሞ ተገቢ የሆኑ መረጃዎችን በማሰባሰብ ለሚመለከተው አካል አቅርበን ክትትል እያደረግን ነው ብለዋል፡፡
አክለውም የግዥ አፈፃፀም፣ የሰው ሃብት ስምሪት፣ የአርሶ አደር ማቋቋምና ልማት፣ የሬጉላቶሪ ሥራ እና የእንስሳት ሃብት ልማት በቅደም ተከተል ለሌብነትና ብልሹ አሰራር ተጋላጭ ናቸው ተብሎ ተለይተው ክትትል እየተደረገ መሆኑን አንስተዋል፡፡
በባለፉት 6 ወራት የግንዛቤ ማስጨበጥ፣ ስልጠና እና የንቅናቄ መድረኮች የተከናወኑ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
አቶ መርጋ ጢጣ የአመራሩ ድጋፍና ክትትል እጅግ በጣም ጥሩ መሆኑን አንስተዋል፤ አያይዘውም ከኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጋር በመሆን ተለይተው በተያዙ የተጋላጭንት ቦታዎችና ተግባራት ላይ ጥናት እያደረጉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ሌላው ሌብነትና ብልሹ አሰራር ቁልፍ ችግር እየሆነ መምጣቱን አንስተው ለአሰራር ምቹ ያልሆኑ ነገሮች (ለምሳሌ ቢሮ) ማሻሻያ እንዲደረግባቸው መደረጉን ጠቅሰው ማሻሻያዎች እስከሚደረጉ ግን ባለው ነባራዊ ሁኔታ በጥብቅ ዲሲፕሊን እየተመራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments