ቅንጅታዊ አሰራር ብልሹ አሰራርን ይከላከላል፡፡
ቅንጅታዊ አሰራር ብልሹ አሰራርን ይከላከላል፡፡
አዲስ አበባ፤ ጥር 19 ቀን 2018 ዓ.ም
የሰርተፍኬሽን ኢንስፔክሽን ኳራንቲንና ሬጉላቶሪ ዘርፍ የ2018 በጀት ዓመት የ6ወር ሪፖርት አፈጻጸም እና የቀሪ 6ወራት እቅድ ከክፍለከተማ ቡድን መሪዎች ጋር ገመገመ፡፡
በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ 6 ወራት የነበሩ ጠንካራና ደካማ ጎኖች ፣ያጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ የመፍትሔ እርምጃዎች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
ከህገ-ወጥ እንስሳት እርድና ሥጋ ዝውውር አንጻር ከቅንጅታዊ ተቋማትና ባለድርሻ ጋር ያሉ ተግባራት በተሻለ ቅንጅትና መግባባት መሰራታቸውና ውጤታማ መሆናቸው፤በቄራ ድርጅቶች የእርድ ቁጥር መጨመሩ እና በግብርና ዘርፍ የተሰማሩ ነባር የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት እድሳት የተደረገላቸው ተቋማትና ቁጥጥርና ክትትል የሚደረግባቸው አገልግሎት ሰጭ ተቋማትን መረጃ ወቅታዊ የማድረግና መልሶ ማደራጀት ስራ መሰራቱን ዶ/ር አስናቀ የሰርተፍኬሽን ኢንስፔክሽንና ሬጉላቶሪ ዳይሬክተር አንስተዋል፡፡
ተናባቢ የሆነ አንድ እቅድ ከዘርፍ እስከ ክፍለ ከተማ ፈጻሚ ድረስ መታቀዱና ተግባቦት መፈጠሩ፣ ከቅንጅታዊ ተቋማት ጋር በጋራ በመሆን የእንስሳሰት እርድና ሥጋ ዝውውር ላይ ለባለድርሻ አካላት፣ለሥጋ መሸጫ ተቋማት ባለቤቶችና ለሉኳንዳ ነጋዴዎች ማህበርና ለሚመለከታቸው አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ማዘጋጀት መቻሉ እና የመሳሰሉት በግማሽ ዓመቱ የታዩ ጠንካራ ጎኖች እንደነበሩ ዳይሬክተሩ አብራርተዋል፡፡
ይሁን እንጅ ሪፖርት በተቀመጠው የጊዜ ገደብ አለመላኩ እና የቆዳና ሌጦ ጥራት ቁጥጥር በአይነት አለመለየቱ በክፍተት የታዩና ለቀጣይ የሚስተካከሉ ጉዳዮች እንደሆኑ በውይይቱ ተነስቷል፡፡
በቅንጅት የሚሰሩ ስራዎችን እና ብልሹ ሰራር ላይ የሚደረጉ ትግሎችን አጠናክሮ ማስቀጠልና በህገወጥ እንስሳት እርድና ሥጋ ዝውውር ላይ የተጀመረውን የቁጥጥር ስራ ባለድርሻ አካላት እና ቅንጅታዊ ተቋማትን በማሳተፍ አጠናክሮ ማስቀጠል የመሳሰሉት የቀጣይ ትኩረት አቅጣቸዎች መሆናቸው ተገለጸ፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments