የሌማት ትሩፋት የንቅናቄ ዕቅድ አፈፃፀምን ውጤት በተጠቃሚዎች ውጤታማነት መለካት ተገቢ ነው፡፡
የሌማት ትሩፋት የንቅናቄ ዕቅድ አፈፃፀምን ውጤት በተጠቃሚዎች ውጤታማነት መለካት ተገቢ ነው፡፡
አዲስ አበባ፤ ጥር 19ቀን 2018 ዓ.ም
የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን እንስሳት ሃብት ልማት ዳይሬክቶሬት በመደበኛና በሌማት ትሩፋት ሥራ የ45 ቀን እቅድ አፈፃፀም ላይ ከክፍለ ከተማና ከወረዳ ባለሙያዎች ጋር ግምገማ አድርጓል፡፡
የእንስሳት ሃብት ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ደጀኔ ጌታቸው በመደበኛና በሌማት ትሩፋት አዲስና ነባር ተጠቃሚዎችን ከማስቀጠል እንዲሁም ከፋሚሊ ቢዝነስ ስራ ዘርፍ አንፃር የታየውን የማዕከልና የክ/ከተማ አፈፃፀም ልዩነት በማነፃፀር የግምገማ ነጥቦችን አስቀምጠዋል፡፡
አያይዘውም የአዲስና የነባር ተጠቃሚዎች የቁጥር ልዩነት ያመጡና ልዩነት ያላመጡ ክፍለ ከተሞችን በመገለጫ በማቅረብ እቅዱንና ክንውኑን አነፃፅረው አቅርበዋል፡፡
ሌላው አዳዲስ ተቋማትን ወደ ስራ ከማስገባት አንፃር ተቋም የለንም፤ 100% አሳትፈናል በሚል የቀረበው ሪፖርት ላይ እንደገና ቢታይ በሚል አስተያየት ሰጥተዋል፡፡
ፋሚሊ ቢዝነስ ልይ በክዋኔ ኦዲት ወቅት በርካታ ክፍተቶች የተገኙ መሆኑን ዶ/ር ደጀኔ ጠቅሰው ይህ በአስቼኳይ መታረም ያለበት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ከሥራ ዕድል ፈጠራ ጋር በተያያዘ የማይናበብ ሪፖርት መኖሩን እና በእንስሳትና በእጽዋት ተለይቶ ያልቀረበ መሆኑን ማሳያ ኮልፌንና ለሚ ኩራን በመጥቀስ በግምገማው ላይ ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡
ሌላው በግምገማው ወቅት ትኩረት የሚሹ ተብለው የተጠቀሱት የኬጅ ስርጭት፣ የንብ ቀፎ፣ የእንቁላል ምርት ካለን የዶሮ መጠን ጋር ማናበብ፣ የወተት ምርት ካለን የላም ቁጥር ጋር ማናበብ ተገቢ መሆኑ በአጽህኖት ተነስቷል፡፡
የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በቀረበው ሪፖርት ላይ ጥያቄና አስተያየት ሰጥተው ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
በክፍለ ከተማ ክላስተር፣ ግሪን ሃውስ፣ መኖ ማቀናባበሪያ፣ የግብርና ምርት መሸጫ ሱቅ እንዲሁም በወረዳ አንድ ሼድና ግሪን ሃውስ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ተገንብተው ሥራ ላይ እንዲውሉ ማድረግ የሚጠበቅ መሆኑን ዶ/ር ደጀኔ ጌታቸው አንስተዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments