የተሻሻለ ዝርያ ያላቸው ላሞችን መጠቀም ለተሻለ ምርትና ምርታማነት ወሳኝ ነው፡፡
የተሻሻለ ዝርያ ያላቸው ላሞችን መጠቀም ለተሻለ ምርትና ምርታማነት ወሳኝ ነው፡፡
አዲስ አበባ፤ ጥር 21 ቀን 2018 ዓ.ም (አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ)
የእንስሳት ልማት እና ልህቀት ማዕከል ከእንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት (LDI) ጋር በመተባበር የተሻሻለ ዝርያ ያላቸው አምስት /5/ ጊደሮች ወደ ማዕከሉ ማስገባቱን ገልጷል።
ጊደሮቹ የመጡት በግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ከሆለታ ምርምር ማዕከል ሲሆን የተመዘገበ የህይወት ታሪክ/Record/ ያላቸውና የተሻሻሉ ዝርያ መሆናቸው ማዕከሉ በቀጣይ ለሚጠበቅበት የዝርያ ማሻሻል ሥራዎች ወሳኝ ግብዓት እንደሚሆኑ ይጠበቃል።
በቀጣይም በማዕከሉ በተለይም በወተት ከብት እርባታ ክላስተር ምርታማ ያልሆኑ የወተት ከብቶችን ምርታማ በሆኑ እና ዝርያቸው የተሻለ በሆኑ ጊደሮች የመተካቱ ሥራ የሚቀጥል መሆኑን ማዕከሉ በሰጠን መረጃ አመላክቷል።
ማዕከሉ ከሌሎች አጋርና ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብርና በቅንጅት የመሥራቱ ውጤት በመሆኑ ለዚህ ተግባር መሳካት ብርቱ ጥረት ላደረጉ በየደረጃው ያሉ አካላት ማዕከሉ ምስጋና የሚያቀርብ መሆኑንም የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
መረጃውን ያደረሰን የእንስሳት ልማት እና ልህቀት ማዕከል ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡-
YouTube ➲ https://bit.ly/4hnxoMs
Telegram ➲ https://bit.ly/4h2cPVT
Facebook ➲ https://bit.ly/4gjsu1M
Tiktok ➲ https://bit.ly/4gdXK2o
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments