የሥጋ ማጓጓዣ ተሽከርካሪዎችን ስታንዳርድ የማስጠ...

image description
- In ሰርተፍኬሽን፣ ኢንስፔክሽን፣ኳራንቲንና ሬጉላቶሪ ዘርፍ    0

የሥጋ ማጓጓዣ ተሽከርካሪዎችን ስታንዳርድ የማስጠበቅ ሥራ በተጠናከረ መንገድ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል፡፡

የሥጋ ማጓጓዣ ተሽከርካሪዎችን ስታንዳርድ የማስጠበቅ ሥራ በተጠናከረ መንገድ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል፡፡
 


አዲስ አበባ፤ ጥር 22 ቀን 2018 ዓ.ም (አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ)


የሥጋ ማጓጓዣ ተሽከርካሪዎችን ስታንዳርድ በማስጠበቅና በመቆጣጠር ጤንነቱ፣ ደህንነቱና ኃይጅኑ የተጠበቀ የሥጋ ምርት ለህብረተሰቡ የሚቀርብበትን አሰራር ዘርግቶ እየሰራ እንደሚገኝ ከሰርተፊኬሽን፣ ኢንስፔክሽን፣ኳራንታይንና ሬጉላቶሪ ዘርፍ የተገኘው መረጃ ያስረዳል፡፡
በግለሰብም ሆነ በማህበራት የተቀመጠውን መስፈርት አሟልተው የሚመጡ የብቃት ማረጋገጫ ወስደው መስራት የሚችሉበት ምቹ ሁኔታ የተፈጠረ መሆኑን ከዘርፉ ያገኘነው መረጃ ያስረዳል፡፡
ለሥጋ ማጓጓዣ ፍቃድ የተሰጣቸው ተሸከርካሪዎች ለተቆጣጣሪው አካል እና ለማህበረሰቡ በግልጽ በርቀት መታየት የሚችል ስቲከር መለጠፉ እንደሚገባቸውም መረጃው ያመለክታል፡፡                                                                                              ይህ በማይሆንበት ሁኔታ ውስጥ በህገ-ወጥ መንገድ ሲሰሩ በሚገኙ የትኛውም አካላት ላይ ኮሚሽኑ አሰራሩን ጠብቆ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን አስተማሪ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድም መረጃው አያይዞ አስቀምጧል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡-
YouTube ➲ https://bit.ly/4hnxoMs
Telegram ➲ https://bit.ly/4h2cPVT
 Facebook ➲ https://bit.ly/4gjsu1M
Tiktok ➲ https://bit.ly/4gdXK2o


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments