የእንስሳት ልማት እና ልህቀት ማዕከሉን እንደ ስ...

image description
- In የእንስሳት ልማት ልህቀት ማዕከል    0

የእንስሳት ልማት እና ልህቀት ማዕከሉን እንደ ስሙ ማድረግ ከሁሉም አመራርና ባለሙያ የሚጠበቅ ተግባር ነው።

የእንስሳት ልማት እና ልህቀት ማዕከሉን እንደ ስሙ ማድረግ ከሁሉም አመራርና ባለሙያ የሚጠበቅ ተግባር ነው።

 

አዲስ አበባ፤ ጥር 17 ቀን 2017 ዓ.ም

 

ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ ወደ ኮሚሽኑ ከመጡበት ዕለት ጀምሮ ለባለፉት ሦስት ሳምንታት ያለምንም እረፍት ሰባት ሃያ አራት የኮሚሽኑን አመራርና ባለሙያዎች ይዘው በመስራት ተቀዛቅዞ የነበረውን የእንስሳት ልማትና ልህቀት ማዕከል የተፈጠሩትን ክፍተቶች በማረም ለተሻለ  ምርትና ምርታማነት ዝግጁ የማድረግ ሥራ እየተሰራ ይገኛል።

 

ሸዶችን፣ ኬጅዎችን፣ የፍሳሽ ማስወገጃዎችን፣ የውሃ አቅርቦትን፣ የግቢውን ጽዳትና ሌሎች መስተካከል የሚገባቸውን ክፍተቶች በማስተካከል እና ለማህበራቱ የሥራ መመሪያ በመስጠት የሁለተኛ ዙር የእንቁላል ጣይ ቄብ ዶሮዎችን የማስገባት ሥራ ተጀምሯል።

 

ከዚህ በፊት የምርት ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ የእንቁላል ጣይ ዶሮዎች መውጣታቸውን ተከትሎ አሁን ተስተካክሎ ለሥራ ዝግጁ ወደሆኑት ሸዶች ወደ 36,000 የሚጠጉ ቄብ ዶሮዎች በመግባት ላይ ናቸው::

 

በዛሬው ዕለትም ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዩ ሽጉጤን ጨምሮ ምክትል ኮሚሽነሮች አቶ ፋሩቅ ጀማል እና ወ/ሮ ሎኮ ዳለቻ፣ የማዕከሉ ኃላፊ ፀጋ ለማ (ዶ/ር) እንዲሁም ሌሎች መካከለኛ አመራሮችና ባለሙያዎች ተገኝተው የእንቁላል ጣይ ዶሮዎቹን የማስገበ ሥራው ተሰርቷል::


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments