የአዲስ አባባ ከተማ ግብርና ሥራ በሀገር አቀፍ...

image description
- In አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን    0

የአዲስ አባባ ከተማ ግብርና ሥራ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለተሞክሮ ቀረበ፡፡

የአዲስ አባባ ከተማ ግብርና ሥራ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለተሞክሮ ቀረበ፡፡
አዲስ አበባ፤ ጥር 23 ቀን 2018 ዓ.ም (አዳማ)
የፌዴራል ግብርና ሚኒስቴር ባዘጋጀው ሀገር አቀፍ የከተማ ግብርና እስትራቴጂ ንቅናቄ መድረክ የአዲስ አበባ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን በከተማ ግብርና አጀማመር፣ የተመራበት አግባብ እና የተገኙ ውጤቶች ዙሪያ ተሞክሮ አቀረበ፡፡
የፌዴራል፣ የክልል ምክትል ፕሬዝዳንቶች፣ የክልል እና የከተማ አስተዳደር የግብርና ቢሮ ኃፊዎች በተገኙበት የከተማ ግብርና እስትራቴጂ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አርሶ አደር እና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዩ ሽጉጤ ተሞክሮ አቅርበዋል።
በመድረኩም ለግብርና እስትራቴጂው መዘጋጀት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማው ላይ የጀመረው የከተማ ግብርና ስራ እና የከተማው ከፍተኛ አመራር ለስራው የሰጡት ትኩረት እንደ ሀገር ሁሉም ክልልሎች ልምድ ሊወስዱበት እንደሚገባ ተመላክቶዋል፡፡
የግብርና ሚኒስቴር ሚንስትር አቶ አዲስ አረጋም በሀገራችን የሚገኙ ከተሞች በከተማ ግብርና የጀመሩትን እንቅስቃሴዎች የበለጠ ለማሳደግ እና በግብርና ምርት ላይ ተጨማሪ አቅም እንዲኖረው ለማድረግ ወጥ የሆነ የአሰራር እስትራቴጂ ማዘጋጀት አስፈላጊ በመሆኑ ግብርና ሚስቴር እስትራቴጃዊን በማዘጋጀት እና የጋራ በማድረግ የስራ ማስጀመር ስራ ተሰርቶዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments