አዲስ አበባ ከሸማችነት ወደ አምራችነት!

image description
- In አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን    0

አዲስ አበባ ከሸማችነት ወደ አምራችነት!

አዲስ አበባ ከሸማችነት ወደ አምራችነት!

አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ጥር 25 ቀን 2018 ዓ.ም (አዲስ አበባ)

አዲስ አበባ ከተማ ተግባራዊ እያደረገች ያለው የከተማ ግብርና ሥራ እጅግ በጣም በርካታ የከተማዋን ነዋሪዎች ከሸማችንት ወደ አምራችነት እያሸጋገረ ይገኛል፡፡

ከተማችን በሌማት ትሩፋት እና በከተማ ግብርና ሥራዎች በበቂ የምርት አቅርቦት ዋጋ ማረጋጋት ብቻ ሳይሆን የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እየሰራች መሆኑን በተግባር እያሳየች ትገኛለች።
 
ከነዋሪዎቿ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ባለፈ በርካታ የግልና የመንግስት ተቋማት ዛሬ ላይ የከተማ ግብርና ሥራ እየተሰራባቸው የምርት ማዕከል ወደመሆን እየተሸጋገሩ ይገኛሉ፡፡

ሌላው በአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የእንስሳት ልማት እና ልህቀት ማዕከል ምርት በማዕከሉና በየክፍለ ከተማው ባሉ የመሸጫ ሱቆች ላይ  በተመጣጣኝ ዋጋ እያቀረበ መሆኑ ለከተማ ግብርናው ውጤታማ መሆን ዓይነተኛ ማሳያ ነው፡፡

በሌላ በኩልም ኮሚሽኑ አርሶ አደሮች ሁለንተናዊ የዕለት ከዕለት ስራቸዉን ከከተማ ልማት ጋራ በማስተሳሰር የግብርና ምርት ማምረት እንዲችሉ እና በተፈጠረላቸው ምቹ ሁኔታ ተጠቅመው ኑሯቸውን በዘላቂነት እንዲያሻሽሉ አስችሏል።

ከተማ ግብርና ባለዘርፈ ብዙ በመሆኑ የከተማዋ የምርት አቅርቦት በከፍተኛ ሁኔታ እንዲጨምር በማድረግ ረገድም ጉልህ አስተዋፆኦ እያበረከተ ይገኛል፡፡ ሌላው የግብርና ምርትና ግብዓት ጥራቱ፣ ኃይጅኑና ደህንነቱ ተጠብቆ ለነዋሪዎቿ እንዲቀርብ ከማድረግ አንፃርም እየተሰራ ያለው ሥራ ቀላል የማይባል ነው፡፡
እየተመዘገበ ላለው ውጤት መምጣት የፌደራል መንግስቱ፣ ከተማ አስተዳደሩ፣ አጋር አካላት፣ የኮሚሽኑ አመራርና ሰራተኞች ከሁሉ በላይ በአስተሳሰብ በእምነት ተቀብሎ ተግባራዊ እያደረገ ያለው የከተማችን ነዋሪ ሚናው ቀላል አይደለም፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments