ይህን ያውቁ ኑሯል?

image description
- In አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን    0

ይህን ያውቁ ኑሯል?

አዲስ አበባ፤ ጥር 25 ቀን 2018 ዓ.ም

ይህን ያውቁ ኑሯል?

ዶሮዎች በዘመናዊ መንገድ ለማረባትና ጥሩ ውጤት ለማግኘት ከተፈለገ በመጠንና በዓይነት ተገቢውን መኖ ማቅረብና የአመጋገብ ስርዓት መከተል ዋነኛ ተግባር ነው፡፡

የንጥረ ምግብ ግይነቶችና ተግባራቸው፡-

1.1.1 ውኃ
ውኃ ከንጥረ ምግቦች ውስጥ ባይመደብም እጅግ በጣም አስፈላጊ  ነገር ነው፡፡ ዶሮዎች የሚሰፈልጋቸው የውኃ መጠን እንደየ አካባቢው የሙቀት መጠን፣ የመኖ ፍጆታ፣ የውኃ ሙቀት፤ የእንቅስቃሴና የምርት መጠን ወዘተ… ይለያያል፡፡ ለዶሮዎች የምነሰጣቸው ውኃ በተቻለ መጠን ንፁህና ያልተበከለ መሆን አለበት፡፡ 

1.1.2 ፕሮቲን
ፕሮቲን አካል ገንቢ ንጥረ-ምግብ ስለሆነ ለአካል ግንባታና ዕድገት፣ ያረጁ ሴሎችን ለመተካት እንዲሁም ዕንቁላል ለማምረት የሚያገለግል ነው፡፡ የዶሮዎች የፕሮቲን ፍላጎት ለመጨመር በአብዛኛው በፕሮቲን ይዘታቸው ከፍተኛ የሆኑ የመኖ ዓይነቶችን በድብልቅ ምግብ ውስጥ በመጨመር  መመገብ አለባቸው፡፡
#የፕሮቲን_መገኛዎች

ፕሮቲን /አካል ገንቢ/ ከእንሰሳት እርድ ተረፈ ምርቶች፡ ከዘይት ጭማቅ ተረፈ ምርቶችና በሌሎች ይገኛል፡፡
ፕሮቲን ከእንሰሳት እርደ ተረፈ ምርቶች ከበሽታ ሥጋ ከተከለከሉ ደረቅ የተፈጨ ደም፣ የተፈጨ ሥጋ፣ የተፈጨ ሥጋና አጥንት፣ እንዲሁም ከደረቅ የተፈጨ ዓሣ ይገኛል፡፡ ከዘይት ጭማቅ ተረፈ- ምርቶች ደግሞ ከጥጥ ፍሬ፣ ከጎመን ዘር፣ ከለውዝ፣ ከሱፍ፣ ከተልባ፣ ከሰሊጥ፣ ከኑግ፣ እንዲሁም ከአኩሪ አተር ፋጉሎ ይገኛል፡

1.1.3 ኃይል ሰጪ

የኃይል ሰጪ ንጥረ ምግብ መጠን የዶሮዎችን የመኖ ፍጆታ ከሚወሰኑ ነገሮች አንዱና ዋነኛው ነው፡፡ ዶሮዎት ዝቅተኛ ኃይል ሰጪነት ያለው መኖ ከተመገቡ በቀን የሚያስፈልጋቸውን ኃይል ለማግኘት ብዙ በመብላት የመኖ ብክነትን ያስከትላሉ፡፡

#የኃይል_ምንጭ_መገኛዎች፡-
የዶሮ መኖ ቅንብር ውስጥ ለኃይል ሰጪነት የሚጠቅሙ የእህል ዓይነቶች እንደ በቆሎ፣ ገብስ፣ ማሽላ፣ ስንዴ፣ አጃ የመሳሰሉት 

1.1.4 ማዕድናት(minerals)
ማዕድናት በዶሮ አካል ውስጥ ብዙ አይነት አገልግሎት ይሰጣሉ፡፡ ማዕድናት ለአጥነት ግንባታ፣ ለዕንቁላል በተለይም ቅርፊቱን ለመሥራት፣ ለጡንቻና ለደም ዝውውር ለመሳሰሉት አገልግሎቶች ይውላሉ፡፡ እነዚህን ማዕድኖች ከተለያዩ የመኖ ምንጮች ማግኘት ይቻላል፡፡ ከጨው፣ ከተፈጨ አጥነት፣ ከአሸዋ እና ከመሳሰሉት ማዕድናት ይገኛሉ፡፡
#የማዕድናት_መገኛዎች

የተፈጨ አጥንት፡- (ካልስየምና ፎስፈረስ)፣ የደረቀ የተፈጨ ስጋና አጥነት-(ካልስየምና ፎስፎረስ)፣ የበረሃ / ድንጋይ /Lime Stone/ ፣ (ካልሰየም)፣ ጨው (ሶድየም ፣ ክሎሪን እና አዮዲን) የማዕድናት መገኛዎች ናቸው፡፡...
ምንጭ፡- ማህበራዊ ሚዲያ


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments