ሰባት ሃያ አራት በተግባር!

image description
- In የእንስሳት ልማት ልህቀት ማዕከል    0

ሰባት ሃያ አራት በተግባር!

ሰባት ሃያ አራት በተግባር!

አዲስ አበባ፤ ጥር 19 ቀን 2017 ዓ.ም

 

በአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የእንስሳት ልማትና ልህቀት ማዕከል የተቋቋመበትን ዓላማ ለማሳካት በርካታ የልማት ሥራዎች እየተሰሩ ይገኛል፡፡

ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ ወደ ኮሚሽኑ ከመጡበት ጊዜ አንስቶ የኮሚሽኑን አመራሮች እና ባለሙያዎች በማስተባበር ሰባት ሃያ አራትን በተግባር እያሳዩ ይገኛሉ፡፡

የማዕከሉን ምርትና ምርታማነት በማሳደግ ማዕከሉ ገበያው ላይ መጫዎት ያለበትን ሚና መጫወት እንዲችል የተፈጠሩ ክፍተቶች በፍጥነት መታረም ስላለባቸው የማስተካከል ሥራ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

አያይዘውም መንግስት እና ማህበረሰቡ ከማዕከሉ የሚጠብቁትን ውጤት በተግባር ማየት እንዲችሉ አመራሩ፣ ባለሙያውና ተጠቃሚዎች ተናበው መስራት አለባቸው ብለዋል፡፡

ኮሚሽነሩ አመራሩን፣ ባለሙያውን እና ማህበራትን ይዘው ማዕከሉን የምርት ማዕከል ለማድረግ አብረው እየሰሩ መሆኑ ለኮሚሽኑ ሰራተኞች እና ለማህበራቱ ትልቅ መነሳሳትን የፈጠረ መሆኑን ያነጋገርናቸው ባለሙያዎች ገልፀውልናል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments