ለውሾች የቅድመ-መከላከል ሕክምና በመስጠት ማህበ...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

ለውሾች የቅድመ-መከላከል ሕክምና በመስጠት ማህበረሰቡን ከውሻ እብደት በሽታ መጠበቅ ይገባል፡፡

ለውሾች የቅድመ-መከላከል ሕክምና በመስጠት ማህበረሰቡን ከውሻ እብደት በሽታ መጠበቅ ይገባል፡፡ 

አዲስ አበባ፣ 27/5/2018 ዓ.ም (አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ)

የውሻ እብደት በሽታን ለመከላከል የክትባት  አጠቃቀም እና አያያዝ ዙሪያ ላይ ለማእከል፣ ለክፍለ ከተማ እና ለወረዳ ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

የውሻ እብደት በሽታ ክስተትና ስርጭትን ቀድሞ ለመከላከል የመከላከያ ክትባት መስጠት አስፈላጊ መሆኑን ዶ/ር ታደሰ ከበደ የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር ከፍተኛ የእንሰሳት ሐኪም ገልጸዋል፡፡

አያይዘውም ማንኛውም ሰው በማንኛውም እንስሳት ላይ የውሻ እብደት በሽታ መኖሩን እንዳዎቀ ወይም ሲጠራጠር፣ በበሽታው ምክንያት ሞት መከሰቱን ካወቀ በአቅራቢያው ለሚገኘው  እንስሳት ጤና ክሊኒክ በፍጥነት ማሳወቅ እንዳለበት አሳስቧል፡፡

ም/ኮሚሽነር መሐመድ ልጋኔ የባለቤት አልባ ውሾች ቁጥር መበራከት አሳሳቢ እየሆነ በመምጣቱ ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት የማህበረሰቡን ንቃተ ህሊና ከፍ የማድረግ ኃላፊነት የሁሉም እንደሆነ አጽህኖት በመስጠት ገልጸዋል፡:      
                      
በመጨረሻ ውሾችን ማከም በተዘዋዋሪ መንገድ ማህበረሰቡን ከውሻ እብደት በሽታ መጠበቅ እንደሆነ ተሳታፊዎቹ  ገልፀው በጋራ ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments