የእንስሳት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የእንስ...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

የእንስሳት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የእንስሳት ሸድ /ቤት/ አሰራር በስታንዳርድ የሚመራ መሆን አለበት።

የእንስሳት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የእንስሳት ሸድ /ቤት/ አሰራር በስታንዳርድ የሚመራ መሆን አለበት።

አዲስ አበባ፤ ጥር 28 ቀን 2018 ዓ.ም (ቢሸፍቱ)

የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ከSNV + Bridge  ፕሮጀክት ጋር በመተባበር የእንስሳት እርባታ ቦታ ዝግጅት ስታንዳርድ ላይ ውይይት አድርጓል።

የኮሚሽኑ ስትራቴጅክ አመራሮች፣ ጉዳዮ የሚመለከታቸው የማዕከል ዳይሬክቶሬቶችና ባለሙያዎች፣ የዘርፉ የክፍለ ከተማ ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣ የSNV+ Bridge ፕሮጀክት አስተባባሪዎችና ባለሙያዎች፣ የአዲስ አበባ የአካባቢ ጥበቃ፣ የመስሪያ ቦታዎች አስተዳደር ኤጀንሲ እና ሌሎች የሚመለከታቸው ሴክተር ተቋማት ተወካዮች በመድረኩ ተሳታፊ ሆነዋል።

ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ ከSNV+Bridge ተቋም ጋር በመሆን ከተማ ግብርናው ላይ ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን አንስተው በተለም ከእንስሳት እርባታ ሸድ አሰራር ጋር በተያያዘ ሸዱን በስታንዳርድ መስራትና ከከተማች እድገት ጋር የሚሄድ ማድረግ የሚገባ መሆኑን ገልፀዋል።

የSNV ፕሮጀክት ማናጀር አቶ ማርኮ ስትሬንግ በበኩላቸው ከኮሚሽኑ ጋር አብረው እየሰሩት ያለው ስራ ጥሩ መሆኑን ገልፀው በቀጣይም የበለጠ አብረው ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የSNV+Bridge የአዲስ አበባ ፕሮጀክት ማናጀር ወ/ሪት ነኢማ ጉልማ፣ የፕሮጀክቱ ሱፐርቫዘር አቶ ትንሳኤ ብርሃኑ እና የካውኔት ካምፖኒ መስራች አቶ አዳነ ጌታሁን የመወያያ ርዕሰ ጉዳዮችን አቅርበዋል።

ተሳታፊዎችም በቀረቡት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ አስተያየትና ጥያቄዎች አንስተዋል።

አያይዘውም ከዲዛይንና ከግንባታ አንፃር ከባዮሴኩሪቲ አጠባበቅ፣ ከውሃ አቅርቦት፣ ከመኖ ዝግጅትና አመጋገብ፣ ከማኔጅመንት አኳያ መሰራት ስለሚገባው ነገር በስፋት አንስተዋል።

በተነሱ ሃሳቦች ላይ የኮሚሽኑ ስትራቴጂክ አመራሮች ሃሳብ ሰጥተዋል። ከተማ ግብርና የበለጠ እየዘመነና ዘላቂ በሆነ መንገድ ምርትና ምርታማነትን እያሳደገ መሄድ ስለሚገባው የከተማዋን ዕድገት የሚመጥን የእንስሳት ሸድ በስታንዳርድ መስራት ተገቢ መሆኑን ገልፀዋል።

ሰነድ አቅራቢዎቹም ወ/ሪት ነኢማ ጉልማ እና አቶ አዳነ ጌታሁን በተነሱ ሃሳቦች ላይ አስተያየትና ምላሽ ሰጥተዋል።

ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ ውይይቱ እጅግ በጣም ጥሩ እንደነበረ ገልፀው ከተማችን አዲስ አበባ ስማርት ሲቲ እየሆነች ያለችበት ወቅት በመሆኑ ከከተማዋ ልማት ጋር አብሮ የሚለማ እና በስታንዳርድ የሚመራ የእንስሳት ሃብት ልማት አስፈላጊ በመሆኑ ሁላችንም የሚጠበቅብንን ኃላፊነት ልንወጣ ይገባል ብለዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments