ጠንካራ የሆነ ቅንጅታዊ ሥራ ውጤታማ ተቋምን ለመ...

image description
- In አስተዳደር ዘርፍ    0

ጠንካራ የሆነ ቅንጅታዊ ሥራ ውጤታማ ተቋምን ለመፍጠር ወሳኝ ነው፡፡

ጠንካራ የሆነ ቅንጅታዊ ሥራ ውጤታማ ተቋምን ለመፍጠር ወሳኝ ነው፡፡

አዲስ አበባ፤ ጥር 29 ቀን 2018 ዓ.ም (አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ)

የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ከቅንጅታዊ ተቋማት ጋር የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያው 6 ወራት የሚዲያና ህዝብ ግንኙነት ሥራዎችን በጋራ ገምግሟል፡፡

የኮሙዩኒኬሽን ሥራዎችን በአጀንዳና በመልዕክት በመምራት አንዱ ተቋም የሌላውን የእኔ ብሎ በጋራ እየተሰራ የተሄደበትን ጥንካሬና ክፍተት በጋራ ማየት ተችሏል፡፡

ም/ኮሚሽነር ፀጋ ለማ (ዶ/ር) በቅንጅት በርካታ ሥራዎችን እየሰራን መሆኑን እና በሚዲያና ህዝብ ግንኙነት ቅኝት ውስጥ አስገብቶ መረጃዎችን ለከተማችን ነዋሪዎች በወቅቱና በጥራት ማድረስ በቀላሉ የማይታይ ጉዳይ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

አያይዘውም በዚህ ልክ በጋራ የሰራነውን የሚዲያና ህዝብ ግንኙነት ሥራ በጋራ መገምገም መቻላችን በቀጣይ ጥንካሬዎቻችንን አጠናክረን በማስቀጠል ክፍተቶቻችንን ፈጥነን እርማት ለመስጠጥ ይጠቅማል ብለዋል፡፡

ከፕላንና ልማት ቢሮ፣ ከደንብ ማስከበር ባለስልጣን፣ ከህብረት ሥራ ኮሚሽን፣ ከመስሪያ ቦታዎች አቅርቦትና አስተዳደር ኤጀንሲ፣ ከንግድ ቢሮ፣ ከሥራና ክህሎት ቢሮ፣ ከፋይናንስ ቢሮ የመጡ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬቶችም መድረኩ እጅግ በጣም አስተማሪ እንደነበረ ገልፀው የከተማ አስተዳደሩን የልማት ሥራዎች ተደራሽ ለማድረግ ተሳስረን መስራት የሚገባ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም በትስስር መስራትን በዚህ ልክ አልነበረም የምናየው የከተማ ግብርና ኮሙዮኒኬሽን ዛሬ ያዘጋጀው መድረክ እና ከአመራሮቹ ጋር ያለው ትስስር ለሁላችንም ልምድ መሆን የሚችል መድረክ በመሆኑ ተምረንበታል ብለዋል።

መድረኩን ያስተባበሩትና የመወያያ ሰነድ ያቀረቡት የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የኮሙዮኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ወንደሸን አካሌ በ6 ወራቱ ውስጥ በትስስር የተሰሩ ሥራዎችን ጥንካሬና ክፍተቶች እንዲሁም በቀጣይ መሰራት ስላለባቸው ጉዳዮች በዝርዝር አንስተዋል።

አያይዘውም ልምድ የመለዋወጥ ባህልን፣ ወጥ የሆነ የመረጃ ልውውጥ፣ የሚዲያ ሞኒተሪንግ ሥራዎች፣ የኮሙዮኒኬሽን ሥራን በመልዕክትና በአጀንዳ መምራት ሥራ በጋራ መስራት የሚጠበቅ መሆኑን አጽህኖት ሰጥተው ገልፀዋል።

የኮሙዮኒኬሽን ቢሮን ወክለው በመድረኩ የተገኙት አቶ ጥበቡ በበኩላቸው መድረኩ አስተማሪ እና ልምድ የሚወሰድበት ሌሎች ተቋማትም ላይ መስፋት የሚገባው መሆኑን ገልፀዋል።

አክለውም መድረኩን ላዘጋጀው አካል ምስጋናቸውን አቅርበው በኮሙዮኒኬሽን ቢሮ በኩል እየተደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክረው የሚሰሩበት መሆኑን ተናግረዋል።

የኮሚሽኑ ዳይሬክቶሬቶችም ከየተቋማቱ የመጡት ባለሙያዎች ያነሷቸው ሃሳቦች ገንቢ መሆናቸውን እና ኮሚሽኑ የሚሰራውን ሥራ ከማስተዋወቅ አንፃር በየሚዲያ ፕላትፎርሞቻቸው ላይ የማስተዋወቅ ስራ እንዲሰሩ አሳስበዋል።

የኮሚሽኑ የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌታሁን አበበ የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን እየሰራ ያለው ሥራ የሰው ልጅ መሰረታዊ ፍላጎት የሆነው የግብርና ምርት አቅርቦት ላይ በመሆኑ ሁላችንንም ስለሚመለከተን ሥራዎቻችንን በማስተዋወቅ እና መረጃን በትኩሱ ተደራሽ ማድረግ ላይ ከእያንዳንዳችሁ ብዙ ስለምንጠብቅ አደራ ማለት እወዳለሁ ብለዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments