ለውጥ የማያቋርጥ የሰው ልጅ የሕይወት ጉዞ ነው፡፡
ለውጥ የማያቋርጥ የሰው ልጅ የሕይወት ጉዞ ነው፡፡
አዲስ አበባ፤ የካቲት 02 ቀን 2018 ዓ.ም ወርቃማ ሰኞ፤ (አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ)
ተግባቦት፣ ተነሳሽነት መፍጠር፣ ድርድር፣ እቅድ፣ ቁጥጥር እና ሁለገብ እውቀት ለለውጥ አስፈላጊ ክህሎቶች መሆናቸውን የፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አለማየሁ ግርማ ተናግረዋል፡፡
በሌላ በኩል ገለልተኛ ታዛቢ መሆን፣ አመቻች መሆን እና ያልተቋረጠ ትምህርት የለውጥ ወኪሎች መሆናቸውን ዳይሬክተሩ አያይዘው ገልፀዋል፡፡
አቶ አለማየሁ ግርማ በወርቃማዋ ሰኞ የእውቀት ሽግግር መድረክ ላይ ለውጥ የማይቀር የሰው ልጅ የሕይወት ጉዞ መሆኑንም አንስተዋል፡፡ በተያያዘም ለውጥ በትክክለኛ መሣሪያ፣ በትክክለኛ መሪ እና በትክክለኛ አመለካከት ሲመራ ትልቅ እድገትን እንደሚያመጣ ተናግረዋል፡፡
ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዩ ሽጉጤ ለውጥ የማያቋርጥ ሂደት በመሆኑ ለውጥን የምንመራበትና የምንይዝበት እውቀት፣ ክህሎትና አመለካከት እንደተጠበቀ ሆኖ ልዩ ጥበብ ያስፈልጋል ብለዋል::
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments