በማዕከሉ ለህብረት ሥራ ማህበራት የግንዛቤ ፈጠራ...

image description
- In የእንስሳት ልማት ልህቀት ማዕከል    0

በማዕከሉ ለህብረት ሥራ ማህበራት የግንዛቤ ፈጠራ ሥልጠና ተካሄደ።

በማዕከሉ ለህብረት ሥራ ማህበራት የግንዛቤ ፈጠራ ሥልጠና ተካሄደ።



አዲስ አበባ፤ የካቲት 03 ቀን 2018 ዓ.ም (አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ)



የእንስሳት ልማት እና ልኅቀት ማዕከል ከአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 የህብረት ሥራ ማህበራት ጋር በመተባበር በማዕከሉ ለተደራጁ የህብረት ስራ ማህበራት የግንዛቤ ፈጠራ ስልጠና ተሰጠ።
ሥልጠናው የተሰጠው ከአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 በመጡት የዘርፉ ባለሙያዎች ሲሆን በሂሳብ መዝገብ አያያዝ፣ በህብረት ሥራ ማህበራት አሠራሮች፣ በኮሚቴው ተግባርና ኃላፊነት ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ግንዛቤ ያስጨበጠ ነው።
በሥልጠናው የተሳተፉትና ቀደም ብለው በእንቁላል ጣይ ዶሮ እርባታ የህብረት ሥራ ማህበራት የተደራጁ አርሶ አደሮች ሥልጠናው ያለባቸውን ክፍተት የሚሞላ በመሆኑ አስፈላጊ መሆኑን በማንሳት ቀጣይነት ያለው በተግባር የተደገፈ ሥልጠና ቢቀጥል እንደሚፈልጉ አንስተዋል።
በማዕከሉ የገበያ ልማት ቡድን መሪ የሆኑት ወ/ሮ ሣራ ንጉሴ በሥልጠናው ማብቂያ በሰጡት ማጠቃለያ ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር መሠል ክፍተት የሚሞሉ ሥልጠናዎች እንደሚቀጥሉና የማህበራትን ተጠቃሚነት ለማሳደግ እንደሚሠራ  አስገንዝበዋል።
መረጃውን ያደረሰን የእንስሳት ልማትና ልህቀት ማዕከል


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments