መልካም አስተዳደር እንዴት ይገለጻል?
መልካም አስተዳደር እንዴት ይገለጻል?
አዲስ አበባ፤ የካቲት 07 ቀን 2018 ዓ.ም
የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የመልካም አስተዳደር ችግሮች እና የቅሬታ ምንጮችን መለየትን በተመለከተ የተደረገውን የዳሰሳ ጥናት ግምገማ አካሂዷል፡፡
መልካም አስተዳደር እያንዳንዱ የፖለቲካ አመራር እንዲሁም የሕዝብ አገልጋይ የህብረተሰቡን ጥቅም በማስቀደም በሕግ የተሰጠውን ሥልጣን፤ መዋዕለ ነዋይ እንዲሁም ድርጅት በኃላፊነት እና በተጠያቂነት መምራት ነው:: በተጨማሪም አሳታፊ፣ ግልጽ እና ተጠያቂነት ላይ የተመሰረተ የአሠራር ሂደት መከተልንም ያመለክታል::
ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ መልካም አስተዳደርን ማስፈን ሲባል የሕግ የበላይነትን መከተል፣ ተጠያቂነትና ግልጽነትን ማስፈን እንዲሁም ለሕዝብ ምላሽ ለመስጠት የሚደረግ ዝግጁነት/ተቆርቋሪነት/ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
መልካም አስተዳደር የሚለው ጽንሰ ሃሳብ በዓለም አቀፍ ደረጃ ስምምነት የተደረሰበት ትርጉም ባይኖርም የሰብዓዊ መብት መከበር፣ የሕግ የበላይነት፣ የዜጎች ውጤታማ ተሳትፎ፣ የባለብዙ ተዋናዮች (የሕዝብ እና መንግሥት) አጋርነት፣ የፖለቲካ ብዝኃነት፣ ግልጽ እና ተጠያቂነት ያለው አሠራር እንደሆነ የጥናት ሰነድ ያቀረቡት ዶ/ር ፋሲካ በለጠ ገልፀዋል፡፡
የኮሚሽኑ ም/ኮሚሽነሮች፣ ዳይሬክቶሬቶች፣ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች በቀረበው የዳሰሳ ጥናት ላይ ቢስተካከል ያሏቸውን አስተያየቶች እና ግልጽ ያልሆኑ ጥያቄዎች አንስተው የጋራ ተደርጓል፡፡
ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ የተነሱት ሃሳቦች ገንቢ በመሆናቸው የጥናት ቡድኑ ወስዶ አስተካክሎ የዳሰሳ ጥናቱን እንዲያቀርብ፣ በዳሰሳ ጥናቱ ግኝት መሰረት የሚመለከታቸው ሥራ ክፍሎች ወስደው ተግባራዊ እንዲያደርጉ አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments