የግዢ ፍላጎት ወቅታዊ ተፈፃሚነት የተቋሙን ሥራ ውጤታማነት ይወስናል፡፡
የግዢ ፍላጎት ወቅታዊ ተፈፃሚነት የተቋሙን ሥራ ውጤታማነት ይወስናል፡፡
አዲስ አበባ፡ የካቲት 09 ቀን 2018 ዓ.ም
የግዢ ፍላጎት ውቀታዊ ተፈፃሚነት የተቋሙን ሥራ ውጤታማነት ከሚወስኑ ጉዳዩች መካካል አንዱ ነው፡፡ወቅቱን ጠብቆ የሚደረግ የፍላጎት ዳሰሳ እና የጨረታ ሂደት የተቋሙን የግብዓት ፍላጎት ከማሟላት ባሻገር የዕቅድ ውጤታማነትንም ይወስናል፡፡
ግዢን በወቅቱ ተፈፃሚ ማድረግ ለተቋሙ ጤናማ የስራ ፍሰትና ለአገልግሎት ተደራሽነት ወሳኝነት ያለው ሲሆን የ2018 የተቋሙ የግዢ ፍላጎት አሰባሰብ እና በኃላፊ አፀድቆ ወደ ጨረታ መግባት ላይ ያለው የጊዜ አጠቃቀም ችግር ያለበት መሆኑን እንደሚያሳይ ወ/ሮ ዋጋዬ ለገሰ ገልፀዋል፡፡
በጊዜ ላይ ተመስርቶ የማይከናወን የግዢ አፈፃፀም ሂደት የሥራ ውጤታማነት እና የተገልጋይ እርካታ ከመቀነሱም በላይ ለብልሹ አሰራር ተጋላጭ የሚያደርግ መሆኑን የእንስሳት ልማት እና ልህቀት ማዕከል የሰው ሃብት ቡድን መሪ አቶ ቶሎሳ ያደቴ በበኩላቸው ተናግረዋል፡፡
የእንስሳት ሃብት ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ደጀኔ ጌታቸው ከመድኃኒት ከኬሚካል፤ ከፅህፈት መሳሪያና ከደንብ ልብስ ጋር ያለው የግዢ መጓተት ከተቋሙ ወሳኝ ተግባራት አፈፃፀም አንፃር ከፍተኛ ጫና የሚያሳድሩ ጉዳዩች መሆናቸውን አበክረው ገልፀዋል፡፡
የግዢ አፈፃፀም ስራዎችን በወቅቱ ተፈፃሚ ለማድረግ በመናበብ ዳይሬክቶሬቶች በተቀመጠው ጊዜ ሰሌዳ ውስጥ በስፔሲፊኬሽን የታገዘ የግዢ ፍላጎትን ያለመስጠት፤ ኃላፊ ወደ ማዕቀፍ ግዢና ወደ ጨረታ ፕሮሰስ የሚሄዱትን ለይቶ በወቅቱ አፅድቆ ያለማውረድ፣ የጨረታና የጥራት ኮሚቴ በሥራ ውጥረት ምክንያት ፈጥኖ ውሳኔ ያለመስጠት፤ የግዢ ስራ ክፍል ፈጥኖ ወደ ስራ በመግባት በዝግጅት ምዕራፍ ተጠናቆ በተግባር ምዕራፍ እቃዎች እየገቡ ስራ ላይ የሚውሉበትን መንገድ አለመከተል የታዩ ችግሮች ሲሆኑ ለዚህም ልማዳዊ አሰራሮችን ማስቀረት እንደሚገባ የግዢ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አመንሲሳ ጋሩማ ተናግረዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments