"በሃገራችን የተፈጠረውን ምቹ የፖለቲካ ምህዳር...

image description
- In አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን    0

"በሃገራችን የተፈጠረውን ምቹ የፖለቲካ ምህዳር በመጠቀም የአድዋን ድል በኢኮኖሚያዊ ብልጽግና ላይ መድገም ከዛሬው ትውልድ የሚጠበቅ የጀግኖች አባቶቻችን አደራ ነው" ዋና ኮሚሽነር ባዮ ሽጉጤ።

"በሃገራችን የተፈጠረውን ምቹ የፖለቲካ ምህዳር በመጠቀም የአድዋን ድል በኢኮኖሚያዊ ብልጽግና ላይ መድገም ከዛሬው ትውልድ የሚጠበቅ የጀግኖች አባቶቻችን አደራ ነው" ዋና ኮሚሽነር ባዮ ሽጉጤ።

አዲስ አበባ፤ የካቲት 09 ቀን 2018 ዓ.ም

የኮሚሽኑ አጠቃላይ አመራሮችና ሰራተኞች 130ኛው የአድዋ ድል በዓልን ምክንያት በማድረግ የፓናል ውይይት አካሄዱ፡፡

"የአድዋ እሴት ለሁለንተናዊ ሃገራዊ ማንሰራራት" በሚል መሪ ኃሳብ የሚከበረውን የድል በዓል አስመልክቶ የተዘጋጀ ሰነድ ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡

በውይይቱ ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ አድዋ ዘመን የማይሽረው በደማቁ የተፃፈ የድል ታሪክ፣ ጀግኖች አባቶቻችን ድንበር ተሻጋሪና ለጥቁር ህዝቦች ሁሉ የነጻነት ቀንዲል የሆኑበት፣ ለእኛ ኢትዮጲያውን ደግሞ የታሪካችንና የነጻነታችን ኩራት መገለጫና በዓለም ሉአላዊነታችንን ያስመሰከርንበት ጉራታችን መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሰነዱን ያቀረቡት ም/ኮሚሽነር ፀጋ ለማ (ዶ/ር) የአድዋ በዓልን ስናከብር ኢኮኖሚያዊ ብልጽግናዋን በማረጋገጥ ከበለጸጉት ሃገራት ተርታ እንደትካተት ሃገራዊ ኃላፊነትና የዜግነት ድርሻችንን መወጣት ዛሬ ላይ ያለን ትውልዶች ከአባቶቻችን የተረከብነው አደራ መሆኑን ለአፍታም መዘንጋት የለብንም ብለዋል።

አያይዘውም መጪው 7ኛው ሃገር አቀፍ ምርጫም ፍትሃዊ፣ዴሞክራሲያዊና ተአማኒነት ያለው ይሆን ዘንድ በአድዋ ድል አንድነት ያስገኘውን ውጤት በመረዳት ከባዳና ባንዳዎች የሚወረወሩ የሃሰት ትርክቶችን  በመዋጋት ዜጎች  ሰላማዊና ግልጽነትን የተላበሰ ሃገርን የሚያሻገር ዴሞክራሲያዊ ምርጫ እንዲያደርጉ የበኩላችንን አበርክቶ መወጣት እንደሚጠበቅብን ተናግረዋል።

ምክትል ኮሚሽነር አቶ መሐመድ ልጋኒ በበኩላቸው የአድዋን ታሪክ ስንዘክር በነጻነት እንድንኖር ያደረጉ አባቶቻችን በደም የከፈሉት ዋጋ መሆኑን በመረዳት ይህ ትውልድ በድህነት ላይ በመዝመት የሃገርን ከፍታ ማጽናት፤ ታሪክን ጠብቆ በተሰማራንበት የስራ መስክ ሃገርን የሚያሻግር የትውልድ አርበኛ በመሆን ከኢኮኖሚ ጥገኝነት ተላቀን በራስ አቅም የመቆም ጽናትን ማረጋገጥ ይገባናል ብለዋል፡፡

የኮሚሽኑ አመራርና ሰራተኞችም በቀረበው ሰነድ ላይ ጥልቅ ውይይድ አድርገዋል። አድዋን በህዳሴ ግድባችን ላይ እውን እንዳደረግነው ሁሉ በቀሪ ሃገራችን በነደፈቻቸው አጀንዳዎች ላይም በተጠየቀው ነገር ሁሉ ቀድመን በመገኘት አድዋን እንደግመዋለን ብለዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments