የእናት ሀገር ህልውና ከእናቶች ሕይወት ጋር በቀጥታ ተዛምዶ አለው።
የእናት ሀገር ህልውና ከእናቶች ሕይወት ጋር በቀጥታ ተዛምዶ አለው።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 09 ቀን 2018 ዓ.ም
የወርቃማዋ ሰኞች የእውቀት ሽግግር፡፡
በፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ሲኔር የፋይናንስ ባለሙያ ወ/ሮ መሰረት አልታዬ ሴት የእናት እና የሀገር ምሳሌ ስትሆን የማያልቅ ዘላለማዊ ፍቅርን በስስት የምትለግሰን የፍቅርን ምንነት መገለጫ ናት፡፡
አያይዘውም ታላቅ ከሚያደርጓት ነገሮች ደግሞ በህይወት ውስጥ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ተጋፍጣ በብልሃት እና አሸናፊነት የምትወጣ ጠንካራ ፍጥረትነቷ ነው ብለዋል፡፡
ሩህሩህነትን ከአፍቃሪነት ጋር ታድላ የተፈጠረች ለወንድ የህይወቱ ማገር እና ምሰሶ ናት። ወንድ ያለ ሴት ሙሉነት እና የህይወት ጣእም የሌለው መሆኑንም አብራርተዋል፡፡
የእናት ሀገር ህልውና ከእናቶች ሕይወት ጋር በቀጥታ ተዛምዶ እንዳለውና የሰመረ ትውልድ ሊቀጥል የሚችለው በጥሩ ሁኔታ በተገነባ የእናቶች አቅም ነው ብለዋል፡፡
ም/ኮ ኮሚሽነር መሀመድ ልጋኒ ዓለም ላይ ያለ ኃላፊነት ሁሉ በሴቶች ትክሻ ላይ ናት ብለው በማጠቃለያ ንግግራቸው አስቀምጠዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments