የተቀናጀ የከተማ ግብርና ስራዎችን በማከናወን ም...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

የተቀናጀ የከተማ ግብርና ስራዎችን በማከናወን ምርታማነትን ለመጨመር በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡

የተቀናጀ የከተማ ግብርና ስራዎችን በማከናወን ምርታማነትን ለመጨመር በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡

አዲስ አበባ፤ የካቲት 10 ቀን 2018 ዓ.ም

በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 10   የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ጽ/ቤት የተቀናጀ የከተማ ግብርና  ስራዎችን በማከናወን ምርታማነትን ለመጨመር በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ቸርነት ሽፈራው   ተናገሩ፡፡

ኃላፊ እንደገለጹት ተመጋጋቢ የሆኑ   የከተማ ግብርና ስራዎችን በስፋት በማከናዎን የጓሮ አትክልት ፣የንብ ማነብ ፣የአሳ እርባታ እና የዶሮ እርባታ ስራዎችን  በማቀናጀት ምርታማነትን በመጨመር የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት እና የአመጋገብ ሰርዓታችንን ሊያሻሉ የሚችል ስራ  በትኩረት እየተሰራ   እንደሚገኝ  ገልጸው ሁሉም ማህበረሰብ  ያሉትን ጸጋዎች በአግባቡ በመጠቀም  ተመጋጋቢ የሆኑ  ስራዎችን  በማቀናጀት የሰርቶ   ማሳያ   ስራዎችን ወደራስ በማስፋት የተቀናጀ የከተማ ግብርና ስራዎችን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments