የእንስሳት ልማት ኢንቲትዩት 100 ዶዝ ፆታው የ...

image description
- In የእንስሳት ልማት ልህቀት ማዕከል    0

የእንስሳት ልማት ኢንቲትዩት 100 ዶዝ ፆታው የተለየ ዘር /Sexed semen) ለማዕከሉ ድጋፍ አደረገ።

የእንስሳት ልማት ኢንቲትዩት 100 ዶዝ ፆታው የተለየ ዘር /Sexed semen) ለማዕከሉ ድጋፍ አደረገ።


አዲስ አበባ የካቲት 10 ቀን 2018 ዓ.ም


የእንስሳት ልማት እና ልኅቀት ማዕከል ከእንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት (LDI) 100 ዶዝ ፆታው የተለየ ዘር (Sexed semen) በድጋፍ መልክ አገኘ።
ማዕከሉ ከሌሎች መሠል መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ጋር በትብብር መስራቱን የቀጠለ ሲሆን ይህ ፆታው የተለየ  ዘር ደግሞ የዝርያ ማሻሻል ስራዎችን ለማቀላጠፍ የወቅቱ ምርጥ ቴክኖሎጂ በመሆኑ ለወተት ከብት እርባታው ዘርፍ ወሳኝ ሚና የሚኖረው ይሆናል።
በማዕከሉ ምርታማ ያልሆኑ የወተት ከብቶችን ምርታማ በሆኑ ከብቶች የመቀየር ሂደቱ የተጠናከረ ሲሆን በዚህ ሂደት ውስጥ ፆታው የተለየ ዘር መጠቀም የዘርፉን ምርታማነት ከማሳደግም በላይ የማዕከሉን ዓላማ ለማሳካት የራሱን ድርሻ ይወጣል።
በዚህ ረገድ የእንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት ለማዕከሉ እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል በማመን አሁን ለተደረገው ድጋፍ ማዕከሉ ላቅ ያለ ምስጋና ያቀርባል።
መረጃውን ያደረሰን የእንስሳት ልማት እና ልህቀት ማዕከል ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡-
YouTube ➲ https://bit.ly/4hnxoMs
Telegram ➲ https://bit.ly/4h2cPVT 
Facebook ➲ https://bit.ly/4gjsu1M
Tiktok ➲ https://bit.ly/4gdXK2o


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments