ወቅቱን ጠብቆ የተዘራ ማሳ ምርትና ምርታማነትን...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

ወቅቱን ጠብቆ የተዘራ ማሳ ምርትና ምርታማነትን በዘላቂነት ያረጋግጣል፡፡

ወቅቱን ጠብቆ የተዘራ ማሳ ምርትና ምርታማነትን በዘላቂነት ያረጋግጣል፡፡

አዲስ አበባ፤11/6/2018 ዓ.ም

የ2017/2018 ምርት ዘመን የመኸር ሰብል ድህረ-ምርት ከማሳ ዝግጅት ጀምሮ በሰብል ካላንደር መሰረት ወቅቱን ጠብቆ በመዘጋጀቱ በማሳ ላይ ካለው ሰብል አቋም እና ምርት በማየት ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ አቶ ተስፋዬ ኪዳነማርያም  የእጸዋት ሰብል ልማት ከ/ባለሙያ

አያይዘውም በምርት ዘመኑ የሰብል ምርት ማሳደጊያ ግብዓት አቅርቦት ሰው ሰራሽ ማዳበሪያ 15,403.25 ኩንታል ለአርሶ አደሩ ተክፋፍሎ ጥቅም ላይ  እንደዋለ እና በተጨማሪ ምርጥ ዘር c1  144 ኩንታል፣ c2 ዘር ከአርሶ አደሩ ተበጥሮ 1,027 ኩንታል ጥቅም ላይ እንደዋለ ገልጸዋል፡፡

ሌላው 7,165 ሄ/ር በዘር የተሸፈነ ሲሆን ከዚ ውስጥ በሰብል ዓይነት ሲታይ ስንዴ 2,175 ሄ/ር፣ ጤፍ 4,649.55 ሄ/ር፣ ሌሎች 325  ሄ/ር፣ ጥራጥሬ 15.5 ሄ/ር መሬት በሰብል እንደተሸፈነና  5,279 አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ማድረግ እንደተቻለ ተናግረዋል፡፡

በ2017/2018 ምርት ዘመን ድህረ-ምርት የተገኘ ምርት በቶን 20,199.68 ሲሆን አፈፃፀሙ 104%፣ በሰብል ዓይነት ሲታይ ደግሞ ስንዴ 91,400 ኩንታል፣  ጤፍ 99,965.33 ኩንታል፣ ጥራጥሬ 933.37 ኩንታል ሌሎች 9,698.09 ኩንታል መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም የእያንዳንዱ ሰብል ምርታማነት ሲታይ ጤፍ 21.5 ኩንታል በሄ/ር፣ ስንዴ 42 ኩንታል በሄ/ር፣ ጥራጥሬ 60 ኩንታል በሄ/ር እና ሌሎች 29 ኩንታል በሄ/ር መሆኑን ከመስክ ግምገማ  ለማወቅ  እንደተቻለ  አቶ ተስፋዬ ገልፀዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments