ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን ለመከላከል ሁሉም ይመለከተኛ...

image description
- In አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን    0

ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን ለመከላከል ሁሉም ይመለከተኛል የሚል አስተሳሰብ መያዝ አለበት።

ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን ለመከላከል ሁሉም ይመለከተኛል የሚል አስተሳሰብ መያዝ አለበት።

አዲስ አበባ፣ የካቲት 12 ቀን 2018 ዓ.ም፣ አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ

የኤች አይቪ ኤዲስ ስርጭት ንቅናቄ በተጨባጭ ዕቅድ በየደረጃው መመራት አለበት፡፡

  በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ለአመራሮቹና ሰራተኞቹ በኤች አይቪ ኤዲስ ስርጭት ዙሪያ ስልጠና ሰጠ፡፡

የኤች አይቪ ስርጭትን የሚጨምሩ አጋላጭ ቦታዎች በስፋት መገኘት እና ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ቡና ቤቶች፣ ግሮሰሪ፣ የእንግዳ ማረፊያዎች፣ ሆቴሎች፣ ማሳጅ ቤቶች፣ ጫት ቤቶች፣ ሺሻ ቤቶች፣ የምሽት መዝናኛ ቤቶች፣ መጠጥ ቤቶች እና ቱሪስቶች የሚዘወተሩባቸው ቦታዎች መኖራቸው ምክንያት መሆናቸውን ከአዲስ አበባ ጤና ቢሮ የመጡት የጤና ባለሙያ የሆኑት አቶ ስንታየሁ ጎሹ ተናግረዋል።

በተጨማሪም  በ2025 እኤአ 40.8 ሚሊዮን ኤች አይቪ በደማችው የሚገኝ ዜጎች በዓለማችን ላይ የሚገኙ መሆኑን ባለሙያው አያይዘው ገልፀዋል።

በማህበረሰቡ ከፍተኛ ተሰሚነት ያላቸውን የሃይማኖት አባቶችና የማህበረሰብ መሪዎች በመጠቀም መገለልና መድልዎ እንዲወገድ፣የኤችአይቪ/ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ላይ የማህበረሰብ ግንዛቤ ማሳደግ አለብን ተብሏል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments