የተሳለጠ የግብዓት አቅርቦት ለምርትና ምርታማነት ቁልፍ ጉዳይ ነው፡፡
የተሳለጠ የግብዓት አቅርቦት ለምርትና ምርታማነት ቁልፍ ጉዳይ ነው፡፡
አዲስ አበባ፤ የካቲት 14 ቀን 2018 ዓ.ም (አዳማ)
በዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ የተመራ ልዑካን ቡድን የአርቢዎችን የመኖ ችግርና ተያያዥ የግብዓት ጉዳይ መነሻ አድርጎ በአዳማ ከተማ ኦዳ የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ ፋብሪካንና የተሻሻሉ የወተት ላም ዝርያ አርቢዎችን የእርባታ ቦታ ጉብኝት አድርገዋል፡፡
የጉብኝቱ ዋነኛ ዓላማ ጥራቱን የጠበቀ፣ በበቂ መጠን፣ በተመጣጣኝ ዋጋ እና አርቢዎች በሚፈልጉት አግባብ ተደራሽ ሊሆን የሚችል አማራጭ የመኖ አቅርቦት የሚገኝበትን አሰራር ለማመቻቸት መሆኑን ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ ገልፀዋል፡፡
የኦዳ የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ጋዲሳ አበራ ፋብሪካው በ1992 እንደተመሰረተ፣ ከ747 በላይ ባለአክሲዮን እንዳለው፣ ከፍተኛ የፋይናንስ አቅም ያለው መሆኑን እና በሰዓት እስከ 10 ቶን ማምረት እንደሚችል ተናግረዋል፡፡
አያይዘውም ጥራት ላይ እንደማይደራደሩ እና “We Protect Your Farm!” የሚል ሞቶ ይዘው እየሰሩ እንደሆነ፣ የማማከርና የስልጠና አገልግሎት እንደሚሰጡም ገልፀዋል፡፡
የጉብኝቱ ተሳታፊ የሆኑ የማዕከል አመራሮች፣ ዳይሬክቶሬቶች እና የክፍለ ከተማ የዘርፉ ጽ/ቤት ኃላፊዎች በጉብኝቱ ደስተኛ መሆናቸውን እና ፋብሪካው የገበያ ትስስር ተፈጥሮለት በተግባር ሊታይ እንደሚገባው ሃሳብ ሰጥተዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments