ብር አታለው የተቀበሉ ግለሰቦች ተያዙ።
በአዲስ አበበ ከተማ አስተዳዳር መሬት ልማትና አስተዳዳር ቢሮ ሰራተኞች ነን ፤አመራሮችን እናውቃለን የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እናሰራላችዋለን በማለት 6360259.09 (ስድስት ሚሊየን ሶስት መቶ ስልሳ ሺ ሁለት መቶ ሃምሳ ዘጠኝ ) ብር አታለው የተቀበሉ ግለሰቦች ተያዙ።
1. ቶማስ ማናዬ ተበጀ
2. ሳሙኤል ኪዳኔ ሃይሌ
3. ፅዮን አበራ ጣፋ
4. ዳዊት መንግሰቱ
5. ሚኪያስ አውላቸው
የተባሉት ግለሰቦች በ2017 ዓ.ም በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 12 አስተዳዳር ክልል ውስጥ የግል ተበዳይ አቶ መሬት ስፋ 3825 ካ.ሜ ላይ የከብት ማደለቢያ አገልግሎት ለማዋል የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ በመሰራት በሂደት ላይ ያለ መሆኑን በማወቅ እኛ የመሬት ልማትና አስተዳዳር ቢሮ አመራር ሹፌር እና ፀሃፊ ነን ፤ አብረናቸዉ ነው የምንሰራዉ ካርታ በአስቸኳይ እናስጨርስልካለን በማለት ከላይ የተገለፀውን የገንዘብ መጠን ከተቀበሉ በኋላ ከአከባቢው በመሰወራቸው በቀረበ ጥቆማ መሰረት በፖሊስ ክትትል ተይዘው በ12/06/2018 ዓ.ም ፍርድ ቤት ቀርበዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments