ስኬት የዕድል ጨዋታ ሳይሆን የአስተሳሰብና የተግ...

image description
- In አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን    0

ስኬት የዕድል ጨዋታ ሳይሆን የአስተሳሰብና የተግባር ውጤት ነው።

ስኬት የዕድል ጨዋታ ሳይሆን የአስተሳሰብና የተግባር ውጤት ነው።

የወርቃማዋ ሰኞ  የእውቀት ሽግግር 

አዲስ አበባ፤ የካቲት 16 ቀን 2018 ዓ.ም

የቅሬታና አቤቱታ አቀባበልና አፈታት ህግ ማማከር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ታደሰ በዳዳ ግብ ይኑርህ፣ ራስህን እመን፣ ትጋት አትተው፣ ከስህተት ተማር፣ ጊዜህን አክብር እና አዎንታዊ አስተሳሰብ ይኑርህ የሚሉት መርሆች ለስኬት አይነተኛ መንገዶች መሆናቸውን ተናግረዋል:: 

አያይዘውም በተናጠል ከምንሰራ በቡድን ሆነን ብንሰራ ከስኬታችን ላይ ባሰብነው ጊዜ መድረስ  እንችላለን ብለዋል፡፡

ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዩ ሽጉጤ ስኬት ዓላማን መረዳት ወይም ግብን ማሳካት መሆኑን ገልፀዋል፡፡ አክለውም ስኬትን ለማምጣት በትጋት ውስጥ ማለፍ አለብን ብለዋል፡፡ አያይዘውም የኮሚሽኑ አመራርና ሰራተኞች እንደ ተቋም ስኬትን ለማምጣት በሙያዊ ሥነ-ምግባርና በዲሲፕሊን መስራት የሚጠበቅ መሆኑን አጽህኖት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments