ባለን ሙያና ሃብት በመስራት ተጠቃሚነታችንን ማረጋገጥ የብልህነት መገለጫ ነው፡፡
ባለን ሙያና ሃብት በመስራት ተጠቃሚነታችንን ማረጋገጥ የብልህነት መገለጫ ነው፡፡
አዲስ አበባ፤ የካቲት 16/6/2018 ዓ.ም
በዙሪያችን ያሉ ሃብቶቻችንን ወደ ውጤት ለመቀየር ያለንበት ሙያና የስራ ድርሻ ሳይገድበን ተፈፃሚ በማድረጋችን ራሳችንንና በዙሪያችን ያለውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ ማድረግ ችለናል፤ በየካ ክፍለ ከተማ የወረዳ 03 አስተዳደር የቤላ ጤና ጣቢያ የጤና ባለሙያዎች፡፡
በየካ ክፍለ ከተማ የወረዳ 03 አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አንድነት ተሸነ አካባቢውን የቃኘ ተጨማሪ ወጪን የማይጠይቅ ውጤታማ የሆኑ የግብርና ልማት ስራዎችን በመስክ ምልከታችን አሳይተውናል፡፡
በምልከታችንም በቤላ ጤና ጣቢያ ውስጥ ለሚገኙ የህክምና ባለሙያዎች የከተማ ግብርና ጠቀሜታን በማስገንዘብ፣ አካባቢውን መሰረት ያደረገ ግብዓትና ቴክኖሎጂ በማቅረብና የኤክስቴንሽን አገልግሎት በመስጠት በጓሮ አትክልትንና በዶሮ ልማት የእንቁላል ምርትን በሰፊው በማምረት ውጤት እንዲሆኑ መደረጉን አቶ አንድነት ገልፀዋል፡፡
የጤና ባለሙያ የሆኑት ሄለን ፀጋዬና መሰረት ወዬሳ የጓሮ አትክልቱና የዶሮ ልማቱ በጤና ጣቢያው በሚገኘው በራሱ በባለሙያው እንክብካቤ የሚሰራ መሆኑን ገልፀው ከግቢው የሚገኘው የምርት ውጤት ካለው የውስጥ ሰራተኛ ተጠቃሚነት በተጨማሪ ለአካባቢው ማህበረሰብ የሚተርፍ ምርት ማግኘት የተቻለ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ከጤና ጣቢያው በተጨማሪ በወረዳ 03 አስተዳር ግቢ የጓሮ አትክልት ልማትና የእንቁላል ጣይ ዶሮ እርባታ ተግባራዊ በማድረግ የአስተዳደሩ ሰራተኞች እና ባለጉዳዮች በሚገኘው ምርት ተጠቃሚ እየሆኑ መሆኑን አቶ አንድነት ገልፀዋል፡፡
ኃላፊው አያይዘውም ከመንግስት ተቋማት በተጨማሪ በግለሰቦች እና በማህበራት ሰፋፊ የከተማ ግብርና ሥራዎች እየተሰሩና ከወረዳው ባለፈ በክፍለ ከተማና በከተማ ደረጃ በሚዘጋጁ ኢግዚብሽንና ባዛሮች ላይ ምርት ለሸማቹ እየቀረበ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments