የእንስሳት በሽታ ከመከሰቱ በፊት  ቅድመ-መከላከ...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

የእንስሳት በሽታ ከመከሰቱ በፊት  ቅድመ-መከላከል  ላይ የተጠና ሥራ  መሰራት አለበት፡፡

የእንስሳት በሽታ ከመከሰቱ በፊት  ቅድመ-መከላከል  ላይ የተጠና ሥራ  መሰራት አለበት፡፡

አዲስ አበባ፤ የካቲት 18/6/2018 ዓ.ም

በ2018  በጀት  ዓመት  የመጀመሪያው መንፈቅ ዓመት በእንስሳት በሽታ መከላከልና ቁጥጥር ላይ በየደረጃው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች መሰጠታቸውን፤ ለተለያዮ እንስሳት ለ2,061,882 ክትባት እና 907,185 የህክምና አገልግሎት  እንዲያገኙ  መደረጉን የእንስሳት በሽታ መከላከልና ቁጥጥር ቡድን መሪ አቶ የሽዳኛ በላይሁን ገልፀዋል፡፡

አያይዘውም  የውሻ እብደት በሽታን ከመከላከል አንፃር 59,871 ያህል ውሾች እንደተከተቡ እና ባለቤት ላላቸው 17,890 ውሾች ምዝገባና ሰርተፍኬት መሰጠቱን ተናግረዋል፡፡ 

ባለቤት የሌላቸውን ውሾች በተመለከተም ባለቤት  እንዲኖራቸው እና  ስለውሻ እብደት በሽታ  አደገኛነት ለህብረተሰቡ  ግንዛቤ  ማስጨበጥ  እንዲሁም የጎዳና ላይ ውሾችን ቁጥር ለመቀነስ የማምከን ስራ እየተሰራ እንደሆነም ቡድን መሪው ገልፀዋል፡፡

ለበለጠ መረጃ፡-
YouTube ➲ https://bit.ly/4hnxoMs
Telegram ➲ https://bit.ly/4h2cPVT
 Facebook ➲ https://bit.ly/4gjsu1M
Tiktok ➲ https://bit.ly/4gdXK2o
ከላይ በተገለጹት አድራሻዎቻችን ይከታተሉን


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments