ማዕከሉ ሞዴልና የምርት ማዕከል እንዲሆን ሰፊ ሥ...

image description
- In የእንስሳት ልማት ልህቀት ማዕከል    0

ማዕከሉ ሞዴልና የምርት ማዕከል እንዲሆን ሰፊ ሥራ እየተሰራ ይገኛል፡፡

ማዕከሉ ሞዴልና የምርት ማዕከል እንዲሆን ሰፊ ሥራ እየተሰራ ይገኛል፡፡

አዲስ አበባ፤ ጥር 19 ቀን 2017 ዓ.ም

በአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የእንስሳት ልማት እና ልህቀት ማዕከል ላይ ተፈጥሮ የነበረውን መቀዛቀዝ በማነቃቃት ማዕከሉን የምርት ማዕከል ለማድረግ ሰፊ ሥራ እየተሰራ ይገኛል፡፡

የኮሚሽኑ አመራርና ሰራተኞችም ማዕከሉ ላይ የታየውን መቀዛቀዝ በማነቃቃት ወደ ሥራ ለማስገባት የበኩላቸውን ሚና እየተወጡ ይገኛሉ፡፡

ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዩ ሽጉጤ፣ ም/ኮሚሽነር አቶ ፋሩቅ ጀማል፣ ም/ኮሚሽነር ወ/ሮ ሎኮ ዳለቻ፣ የማዕከሉ ኃላፊ ፀጋ ለማ (ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮችና ባለሙያዎች ሰባት ሃያ አራት ማዕከሉ ላይ እየሰሩ ይገኛሉ፡፡

የእንቁላል ጣይ ዶሮ ኬጂ ዝግጅት፣ የግቢና የሼዶች ጽዳት፣ የፍሳሽ ማስወገጃ ትቦዎች ጽዳትና ጥገና፣ የመሰረተ ልማት ማስተካከልና ጥገና፣ የግብዓት አቅርቦት ማመቻቸት (በተለይ የውሃ አቅርቦት)፣ የእንቁላል ጣይ ዶሮ፣ የወተት ላም እና የሚደልቡ ሰንጋዎች ግዥ፣ ለማህበራቱ ጥብቅ የሆነ የሥራ መመሪያ እና ግንዛቤ የመስጠት ተግባራት ወዘተ በስፋት እየተሰሩ ይገኛል፡፡

በሥራ ላይ የሚገኙት አመራሮች፣ ባለሙያዎችና ተጠቃሚዎች ማዕከሉ ሞዴልና የምርት ማዕከል እንዲሆን ጠንክረው እየሰሩ መሆኑን ሁሉም በየበኩላቸው ገልፀዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments