ተማሪዎች በግብርናው ዘርፍ ያላቸውን ዕውቀት በተግባር ማስደገፍ አስፈላጊ ነው።
አዲስ አበባ፤ (የካቲት 19/2018 ዓ.ም)
ተማሪዎች በፅንሰ ሃሳብ ደረጃ የተማሩትን ትምህርት በተግባር በማስደገፍ ዝንባሌያቸውን መለየት አስፈላጊ ነው።
በዛሬው ዕለት በማዕከላችን ተገኝተው ጉብኝት ያደረጉት የቪዥን አካዳሚ ተማሪዎች በማዕከሉ እየተከናወኑ ባሉት ተግባራት መደነቃቸውንና መደሰታቸውን ገልፀዋል።
እንደ ጎብኚዎች ገለፃ የማዕከሉ ሠራተኞችና ማህበራት በዚህ ሁሉ የማምረት ሂደት አልፈው ምርቱን ለማህበረሰቡ ማቅረብ በመቻላቸው ያላቸውን ምሥጋና አቅርበዋል።
የቪዥን አካዳሚ ርዕሰ መምህር የሆኑት አቶ ተስፋዬ ሴታ በገለፃቸው በማዕከሉ በተለይም በእንቁላል ጣይ ዶሮ እርባታ፣ በዳልጋ ከብት ማድለብ እና በወተት ከብት እርባታ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን በመጎብኘታቸው መደሰታቸውን በትምህርት ቤታቸው ስም አመስግነዋል።
በእንስሳት ልማት እና ልኅቀት ማዕከል የዶሮ ሃብት ልማት ባለሙያ የሆኑት አቶ መካሻ መለሠ ተማሪዎች በማዕከሉ ካስተዋሉት ችግር መነሻ በማድረግ በቀጣይ መፍትሄ የማመንጨት የቤት ሥራ እንዳለባቸው አንስተዋል።
በመጨረሻም በማዕከሉ የእንስሳት እርባታ፣ ተዋፅኦና መኖ ልማት ቡድን መሪ የሆኑት አቶ አንዱዓለም ኃ/ማርያም ከተማሪዎቹ የተነሱ ጥያቄዎችን ምላሽ በመስጠት እንደ አስተያየት የተነሱ ሃሳቦችም ወስደው እንደሚያስተካክሉ ገልፀዋል።
የመረጃ ምንጫችን፡- የእንስሳት ልማት እና ልህቀት ማዕከል ነው
ለበለጠ መረጃ፡-
YouTube ➲ https://bit.ly/4hnxoMs
Telegram ➲ https://bit.ly/4h2cPVT
Facebook ➲ https://bit.ly/4gjsu1M
Tiktok ➲ https://bit.ly/4gdXK2o
ከላይ በተገለጹት አድራሻዎቻችን ይከታተሉን
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments