"ተረጂነትንና ልመናን በማስወገድ የራስን የምግብ...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

"ተረጂነትንና ልመናን በማስወገድ የራስን የምግብ ሉዓላዊነት ማረጋገጥ የዘመኑ አርበኝነት ነው"

"ተረጂነትንና ልመናን በማስወገድ የራስን የምግብ ሉዓላዊነት ማረጋገጥ የዘመኑ አርበኝነት ነው"
 አቶ ሞገስ ባልቻ:- በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ  ቅርንጫፍ  ጽ/ቤት ኃላፊ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 19 ቀን 2018 ዓ.ም

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር 4ኛ ዓመት የ3ኛ ዙር የሌማት ትሩፋት ንቅናቄ መርሃ-ግብር ለ300 አዳዲስ የከተማ ግብርና ተጠቃሚ አባወራዎች እና እማ ወራዎች የዶሮ ኬጅና ግብዓቶችን የከተማና ክፍለ ከተማ ከፍተኛ አመራሮች  በተገኙበት የስርጭት  መርሃ-ግብር  አካሂዷል ።

በመርሃግብሩ  ላይ ተገኝተው  መልዕክት  ያስተላለፉት በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ  ቅርንጫፍ  ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት  አቶ ሞገስ ባልቻ ተረጂነትንና ልምናን በማስወገድ  የራሳችን የምግብ ሉዓላዊነት ማረጋገጥ የዘመኑ አርበኝነት መሆኑን ገልፀው አዲስ አበባ  ሸማች ብቻ ሳትሆን አምራች  በመሆን የከተማው ነዋሪ ባለው ይዞታ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የገበያ ጉድለትን  መሙላት ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ  ይገኛል  ብለዋል።

አቶ ሞገስ አክለው ከተማው የሌማት ትሩፋት ስራዎች የስራ ባህልን የመቀር ፣የራስን የምግብ ፍጆታ ማሟላትና የምርት አቅርቦትን ከማሰደግ አኳያ  ውጤታማ ስራዎች  እየተሰሩ እንደሚገኙና የለሚ ኩራ ክፍለ በሌማት ትሩፋትና በሌሎች የልማት ስራዎች ያሉ ፀጋዎችን በአግባቡ  በመጠቀም ማሳያ የሆነች ክፍለ  ከተማ ሆናለች ብለዋል። 
የአዲስ አበባ  ከተማ አርሶ አደርና የከተማ ግብርና  ኮሚሽን  ኮሚሽነር  ባዩ ሽጉጤ  በበኩላቸው የሌማት ትሩፋትና የከተማ ግብርና ስራ የዜጎችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት በተግባር እያረጋገጠ እንደሚገኝ ገልፀው ለከተማው  ነዋሪዎች የአመለካከት  ለውጥ ጭምር በማምጣት አሁን ላይ ከ1.2 ሚሊዮን  በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ  ማድረግ  ችለናል ብለዋል ።

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ  አቶ አድማሱ ደቻሳ እንዳሉት እንደ ክፍለ ከተማ በመደመር መንግስት  ለዘርፎች እመርታ በክብሩ  ጠቅላይ ሚኒስትር  ዶ/ር አብይ አህመድ የተቀመጡ  ኢኒሼቲቭ  ግቦችን ለማሳካት  በርካታ ተግባራት  እየተከናወኑ  እንደሚገኙ ገልፀው  በዛሬው እለትም ለ889 ዜጎች ቋሚና አስተማማኝ ስራ መፍጠር የተቻለበትና በሁሉም  መስክ ለዜጎች ተጠቃሚነትን ለማሳደግ  የሚሰሩ ስራዎች  አጠናክረን  እንቀጥላለን  ብለዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments