ውሃ ለአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ዋነኛው ግብዓት...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

ውሃ ለአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ዋነኛው ግብዓት ነው።

አዲስ አበባ፤ የካቲት 21 ቀን 2018 ዓ.ም

የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን በከተማ ግብርና ሰርቶ ማሳያና ግብዓት ብዜት ማዕከል ያለውን የግብርና ልማት ውጤታማ ለማድረግ የውሃ ልማት ፕሮጀክት እያሰራ ይገኛል።

ፕሮጀክቱን የኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ውል ገብቶ እየሰራ መሆኑን በመስክ ምልከታችን ተመልክተናል።

የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ ፕሮጀክቱ በአጠረ ጊዜ ሥራው ተጠናቆ ወደ ሥራ መገባት ያለበት መሆኑን አጽህኖት ሰጥተው አቅጣጫ ሰጥተዋል።

የውሃ ቁፋሮው ሲካሄድ 63 ሜትር ላይ ውሃ የተገኘ ሲሆን ጠቅላላ ሥራው ሲጠናቀቅ የጉድጓዱ ጥልቀት 411 ሜትር የሚሆን መሆኑን የከተማ ግብርና ሰርቶ ማሳያና ግብዓት ብዜት ማዕከል ሥራ አስኪያጅ አቶ አብደታ ደሜ ተናግሯል።

ሥራ አስኪያጁ አያይዞም ሥራው ሲጠናቀቅ እስከ 20 ሊትር/ሰከንድ ውሃ ማግኘት እንደሚቻል ገልጿል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments