ሥራዎችን በየደረጃው እየገመገሙ መሄድ አንዱ የአ...

image description
- In አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን    0

ሥራዎችን በየደረጃው እየገመገሙ መሄድ አንዱ የአመራር ስልት ነው።

አዲስ አበባ፤ የካቲት 21 ቀን 2018 ዓ.ም

ኮሚሽኑ በመደመር መንግስት 6ቱ ግቦች ላይ የተሰሩ ሥራዎችን አፈፃፀም ግምገማ አደረገ።

እንደ ኮሚሽን በ6ቱ የመደመር መንግስት ግቦች የታቀዱ ተግባራት አፈፃፀም በታቀደው አግባብ እየተሰራ መሆኑ በግምገማው ታይቷል።

ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ ምርትና ምርታማነትን በእጥፍ በማሳደግ ከተማው ከእኛ የሚጠብቀውን የኑሮ ውድነት የማረጋጋትና የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ተልዕኮ በቁርጠኝነት ልንወጣ ይገባል ብለዋል።

ም/ኮምሽነር አቶ መሐመድ ልጋኒ በ6ቱ ግቦች ላይ የታቀዱ ዕቅዶችን አፈፃፀም ማዕከል በማድረግ ከማዕከል እስከ ወረዳ ግምገማ እየተደረገ ግብረ-መልስ በየሳምንቱ እየተሰጠ መሆኑን ተናግረዋል።

የግብርና ምርትና ግብዓት ጥራት፣ ኃይጅንና ደህንነት የማረጋገጥ ሥራ ከመደበኛው አሰራር በተለየ መልኩ በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜት እየተሰራ መሆኑን ም/ኮሚሽነር ፀጋ ለማ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎችም የነበረው የግምገማ ሂደት ተገቢነት ያለው መሆኑን እና ሰፊ ትምህርት የተወሰደበት በመሆኑ የተሰጠንን ኃላፊነት ለመወጣት በጊዜ የለኝም መንፈስ እንሰራለን ብለዋል።

ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ 6ቱን የመደመር መንግስት ግቦች በታቀደው አግባብ ተፈፃሚ ለማድረግ በየደረጃው ያለው አመራርና ባለሙያ በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባው እና ችግር ካሉም በየደረጃው ተጠያቂነትን ማረጋገጥ እንደሚገባ አጽህኖት ሰጥተው ተናግረዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments