እስከ 80 ኪ.ግ ክብደት ያለው የፍየል ዝርያ የማዳቀል ሙከራ በንፋስ ስልክ ላፍቶ!
እስከ 80 ኪ.ግ ክብደት ያለው የፍየል ዝርያ የማዳቀል ሙከራ በንፋስ ስልክ ላፍቶ!
አዲስ አበባ፤ የካቲት 23 ቀን 2018 ዓ.ም
የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ካባ መብራቱ ከሌሎች አመራሮች ጋር በመሆን እስከ 80 ኪ.ም ድረስ የሚመዝኑ የቦርጎት" ዝርያ ያላቸው ፍየሎችን በማዳቀል የሚያረባ ድርጅትን ጎብኝተዋል።
ድርጅቱ ኤልቦድ ትሬዲንግ የሚባል ሲሆን የደበብ አፍሪካ ቦርጎት ዝርያ ያላቸውን ፍየሎች በሀገራችን ለማስፋት እያዳቀለ በማርባት የምርምር ስራ እየሰራ የሚገኝ ነው።
ይህ ድርጅት በሰውሰራሽ የማዳቀል ሳይንሳዊ ዘዴ ፍየሎችን በማዳቀል በሚፈጠር ሂደት እስከ 80 ኪ ግራም የሚመዝኑ እና ጥሩ ምርት የሚሰጡ የፍየል ዝርያዎችን በማዳቀል በማርባት ላይ ይገኛል።
በተመሳሳይ ኮኮክ የተባሉ የዶሮ ዝርያዎችን ከሎካል የዶሮ ዝርያዎች ጋር በማዳቀልና በማርባት የምርምር ስራ እየተሰራ ነው።
ይህንኑ በምርምር ላይ የሚገኘውን ተሞክሮ የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ካባ መብራቱ ከሌሎች አመራሮች ጋር በመሆን ጎብኝተዋል።
የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ካባ መብራቱ በጉብኝት ወቅት እንዳሉት:- እንዲህ አይነት የምርምር ስራዎች ለሀገር ያላቸው ጥቅም የጎላ መሆኑን አንስተው እንደ ክፍለ ከተማ ተገቢን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል።
መረጃውን ያደረሰን የን/ላ/ክ/ከ/አ/አ/ከ/ግ/ል/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙላት ናቸው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments