የእንስሳት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ጠንካራ...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

የእንስሳት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ጠንካራ የባዮሴክዩሪቲ ሥራ መስራት ይገባል፡፡

አዲስ አበባ፤ የካቲት 25 ቀን 2018 ዓ.ም

ኮሚሽኑ ከማዕከል እስከ ወረዳ ላሉ የእንስሳት ሃብት ልማት ቡድን መሪዎች የእንስሳት ጤና ኤክስቴንሽን አገልግሎት አሰጣጥ (የበሽታ ቅድመ-መከላከል ሥራ) ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

ም/ኮሚሽነር አቶ መሐመድ ልጋኒ የእንስሳት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በሽታን ለመከላከል የእንስሳት የጤና ኤክስቴንሽን ትግበራ ከመቸውም ጊዜ በላይ አሁን ተጠናክሮ ተግባራዊ መደረግ ያለበት መሆኑን ገልፀዋል።

መንግስት ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ በነደፋቸው የተለያዩ ኢኒሼቲቮች (የሌማት ትሩፋት) አመርቂ ውጤቶች መገኘታቸውንም ተናግረዋል። አያይዘውም በተለይም ከዶሮ እርባታ ጋር በተያያዘ ጠንካራ የባዮሴክዩሪቲ ሥራ መሰራት ያለበት መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ዶ/ር ደጀኔ ጌታቸው በበኩላቸው የእንስሳት ሃብት የሚፈለገውን ጥቅም እንዳይሰጥ ተግዳሮት ሆነው ከቆዩ ችግሮች መካከል የእንስሳት በሽታ መሆኑን ጠቅሰው፤ የተዘጋጀው ስልጠና በሽታን በመከላከል የሚገኘውን ፋይዳ እንደሚያሻሻል ጠቅሰዋል።

ሌላው ከግብርና ሚንስቴር የመጡት ዶ/ር ጋሻውና ዶ/ር ናን ቦኒ በዘርፉ የተሰማሩ ባለድርሻ አካላትና አጋር ድርጅቶችም የእንስሳት በሽታን በጋራ በመከላከል በኩል ተቀናጅተው ሊሰሩ እንደሚገባ ገልፀዋል።

ዶ/ር ደጀኔ ጌታቸው በምግብ ራስን ለመቻል የሚደረገውን ጥረት ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ የእንስሳት ጤና ኤክስቴንሽን ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በሌላ በኩል በቅርቡ ከዶሮ በሽታ ጋር በተያያዘ እየታየ ያለውን ምልክት ቀድሞ በመቆጣጠር የምርት ዕድገት ላይ የሚፈጠረውን አሉታዊ ተጽዕኖ መግታት ይገባል ብለዋል፡፡ 

በተጨማሪም እንስሳትን ከበሽታ ለመከላከል ክትባት (Vaccination) መስጠት፣ ባዮሴክዩሪቲ (Biosecurity) ተግባራዊ ማድረግ፣ የንጽህና አጠባበቅ እና ተንከባካቢዎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ማድረግ ከእንስሳት ለሚገኘው ምርት ዕድገት ወሳኝ በመሆኑ እያንዳንዳችን ሙያዊ ግዴታችንን ልንወጣ ይገባል ብለዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments