ኮሚሽኑ በ9 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ሲታይ ዘርፈ ብዙ ውጤቶችን አስመዝግቧል፡፡
ዜና ትንታኔ
ኮሚሽኑ በ9 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ሲታይ ዘርፈ ብዙ ውጤቶችን አስመዝግቧል፡፡
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 07 ቀን 2018 ዓ.ም
በ2018 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት ተግባራት አፈፃፀም ኮሚሽኑ ተልዕኮውን ከመወጣት አንፃር በሰራቸው ሥራዎች ዘርፈ ብዙ ውጤቶችን ማስመዝገብ ተችሏል፡፡
በአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን በበጀት ዓመቱ በተያዘው እቅድ መሰረት የከተማውን ማህበረሰብ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለመፍታት በየደረጃው ያለ አመራርና ባለሙያን በንቃት በማሳተፍ የተከናወኑት ተግባራት የተቋሙን ተልዕኮ ውጤታማ ያደረጉ ተግባራት መሆናቸው በ9ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ማረጋገጥ ተችሏል፡፡
የተቋም ግንባታና የአገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነት ከማሳደግ አንፃርም 7ዋና ዋና አገልግሎቶችና 34 ንዑሳን አገልግሎቶች ስታንዳርዳቸውን ጠብቀው ተግባራዊ የተደረጉ መሆኑን ሪፖርቱ ያመለክታል፡፡
ሌላው በብዙሃን መገናኛ፣ በሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን በኩልም ዘርፈ ብዙ የሆነ የተግባቦት ሥራ መሰራቱን ሪፖርቱ በዝርዝር አስቀምጧል፡፡
አርሶ አደሮች ከከተማዋ ልማት ጋር አብረው እንዲለሙ ከማድረግ ጋር በተያያዘ ሕግን፣ ደንብና መመሪያን መሰረት በማድረግ በፍትሐዊነት አገልግሎት መስጠት ተችሏል፤ ቅሬታና አቤቱታዎችንም በመርህ ላይ ተመርኩዞ ምላሽ የመስጠትና በኮሚሽኑ በኩል መታየት የሌለባቸውን ደግሞ ለይቶ ድጋፍ የመስጠት ሥራ በስፋት ተሰርቷል፡፡
ተቋማዊ አቅም ግንባታ ሥርዓት በመዘርጋት የሰራተኛውን የመፈፀምና የማስፈፀም አቅም ለማጎልበት ቲወሬቲካል እና ተግባር ተኮር ስልጠናዎችን በየዘርፉ መስጠት ተችሏል፡፡
ሌላው የከተማ ግብርና ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትና የማረጋገጥ ድርሻን በማሳደግ ረገድ ነባር ተጠቃሚዎችን፤አዲስ የቤተሰብ ፍጆታ ተሳታፊዎችን በእንስሳትና በእፀዋት ስራ ዕድል የተፈ ጠረላቸው ተሳታፊዎች 1,214,525 ማድረስ የተቻለ ሲሆን በተቋም ደረጃ 2,722 በግብርና ስራ በማስቀጠል ከባለፉት ጊዜያት የተሻለ አፈፃፀም መኖሩ በሪፖርቱ ቀርቧል፡፡
የእንስሳት ክትባትና ህክምና ከ100% በላይ አገልግሎት መስጠት መቻሉንና የውሾች ክትባት 96% ተፈፃሚ መደረጉን፣ በሰው ሰራሽ ዘዴ በማዳቀል የወተት ከብት ዝርያ ከማሻሻል አንፃር 91%ማሳካት የተቻለና ሥራዎች በቴክኖሎጂ ተደግፈው እየተሰሩ መሆኑ በሪፖርቱ ተገልጷ፡፡
የግብርና ምርት ግብዓትና አገልግሎት ቁጥጥር አሰራርን በማሻሻል የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ አንፃር በ3ቱ ቄራ ድርጅቶች ውስጥ 268,291/96%/ የእንስሳት ቅድመና ድህረ እርድ ምርመራ ታቅዶ 268,231 ተፈፃሚ ማድረግ መቻሉም በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡
ሌላው የአትክልትና ፍራፍሬ ችግኞችን ስርጭት ከማሳደግ አንፃር የተሻሻሉ የአትክልት ችግኞችን ማዘጋጀትና ማሰራጨት ከ100% በላይ ተፈፃሚ ተደርጓል፡፡
በአጠቃላይ በበጀት ዓመቱ የተገኘውን ውጤት ማስቀጠል፣ ተንጠባጥበው የቀሩ ሥራዎችን በእጥፍ መፈፀም፣ የቁልፍ እና ዐበይት ተግባራትን አስተሳስሮ መስራት፣ ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር፣ የተገልጋይን ቅሬታና አቤቱታ ሙሉ በሙሉ መፍታት እንደሚገባ በዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ አማካኝነት አቅጣጫና የሥራ መመሪያም ተሰጥቶበታል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments