ጥራቱ፣ ደህንነቱና ኃይጅኑ የተጠበቀ የግብርና ም...

image description
- In አስተዳደር ዘርፍ    0

ጥራቱ፣ ደህንነቱና ኃይጅኑ የተጠበቀ የግብርና ምርት ለማህበረሰቡ እየቀረበ ይገኛል፡፡

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 10 ቀን 2018 ዓ.ም (አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ)


በቄራዎች ውስጥ የተከናወነው የእንስሳት እርድ ምርመራ አገልግሎት በከፍተኛ ቁጥር እየተከናወነ ይገናል፡፡ ጥራቱ፣ ደህንነቱና ኃይጅኑ የተጠበቀ የግብርና ምርት ለማህበረሰቡ እንዲቀርብ በመደረጉ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገብ ተችሏ፡፡


ሕገ-ወጥ የእንስሳት እርድን ለመቆጣጠር በተደረገ ኦፕሬሽን የተወሰዱ እርምጃዎች ከባለፈው 2017 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ መሻሻል የታየበት ሆኖ ተመዝግቧል፡፡


አዳዲስ የብቃት ማረጋገጫ የወሰዱ ድርጅቶች ቁጥር ከባለፈው 2017 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት አፈፃፀም ጋር ሲነፃፀር ከ343 ወደ 484 አድጓል። ይህም በግብርናው ዘርፍ ኢንቨስት የሚያደርጉ አካላት መጨመራቸውን ያሳያል። በተጨማሪም የፈቃድ ዕድሳት አፈጻጸም 103% በማሳካት ከባለፈው ዓመት የተሻለ ውጤት አስመዝግቧል።


ድርጅቶች ላይ የተደረገው መደበኛ ክትትል ከባለፈው 2017 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ397 ድርጅቶች ብልጫ አሳይቷል። ይህ የሚያሳየው የጥራት ቁጥጥር ስራው ይበልጥ ተጠናክሮ የቀጠለ መሆኑን ነው፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments