ከ2,722 በላይ ተቋማት የከተማ ግብርና ሥራዎችን እያከናወኑ ይገኛሉ፡፡
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 12 ቀን 2018 ዓ.ም (አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ)
የከተማ ግብርና ልማት ሥራን ከ2,722 በላይ የሆኑ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት እየተገበሩ ይገኛሉ፡፡
የ2018 በጀት ዓመት የ9 ወራት ሥራ ግምገማ ሪፖርት እንደሚያሳየው 759 ት/ቤቶች (በመንግስት 395 በግል 364)፣ 149 ጤና ተቋማት (በመንግስት 108 እና በግል 41)፣ 28 የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች፣ 626 የመንግስት መ/ቤቶች፣ 271 የሃይማኖት ተቋማት፣ 135 የፌዴራል ተቋማት፣ 24 የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ 376 የግል ድርጅቶች፣ 116 መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና 189 ዕድሮችን በከተማ ግብርና ሥራ ማስቀጠል ተችሏል፡፡
ይህ ልምድና ተሞክሮ ለሌሎችም እየሰፋ ያለ በመሆኑ ከዚህ በላይ ውጤት ማስመዝገብ የሚቻልበት ሰፊ ዕድል መኖሪን እና ተቋማት የከተማ ግብርና ምርት ማዕከል እንደሚሆኑ ማሳያ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡-
YouTube ➲ https://bit.ly/4hnxoMs
Telegram ➲ https://bit.ly/4h2cPVT
Facebook ➲ https://bit.ly/4gjsu1M
Tiktok ➲ https://bit.ly/4gdXK2o
ከላይ በተገለጹት አድራሻዎቻችን ይከታተሉን፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments