የልማት ተነሺ አርሶ አደሮችን መልሶ የማቋቋም ሥ...

image description
- In አርሶ አደር ልማትና መልሶ ማቋቋም ዘርፍ    0

የልማት ተነሺ አርሶ አደሮችን መልሶ የማቋቋም ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 12 ቀን 2018 ዓ.ም (አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ)


በተያዘው የ2018 በጀት ዓመት ባሳለፍነው 9 ወራት ውስጥ የሥራ አፈፃፀም ግምገማው እንደሚያሳየው 473 የልማት ተነሺ አርሶ አደሮችን በመልሶ በማቋቋም የፋይናንስ ድጋፍ እንዲያገኙ በማድረግ ወደ ሥራ ለማስገባት ታቅዶ 473ቱንም (100%) በ86 ማህበራት በማደራጀት ወደ ሥራ እንዲገቡ ተደርጓል፡፡

ለዚህም አጠቃላይ የተደረገ የቀጥታ ፋይናንስና የተዘዋዋሪ ብድር ብር 98,568,487.00 ድጋፍ መደረጉን ከሪፖርቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ 

የ9 ወራት ሥራ አፈፃፀሙ እንደሚያሳየው የሥራ ዕድል ከመፍጠር አንፃርም 4,925 የልማት ተነሺ አርሶ አደሮችን በመለየት ግንዛቤ መፍጠር ተችሏል፤ እንዲሁም 727 በቴክኒክና ሙያ ተቋማት ውስጥ በማስገባት ሙያዊ ስልጠና እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡

ይህ ቀጣይነት ያለው መንግስት ልዩ ትኩረት በመስጠት አርሶ አደሩ ከከተማው ልማት ጋር አብሮ እንዲለማ እየተሰራ ያለ አመርቂ ውጤት እየተመዘገበበት የሚገኝ ጉዳይ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ፡-
YouTube ➲ https://bit.ly/4hnxoMs
Telegram ➲ https://bit.ly/4h2cPVT
 Facebook ➲ https://bit.ly/4gjsu1M
Tiktok ➲ https://bit.ly/4gdXK2o
ከላይ በተገለጹት አድራሻዎቻችን ይከታተሉን፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments