የግብርና ምርት ጥራት፣ ኃይጅንና ደህንነት ማስጠ...

image description
- In ሰርተፍኬሽን፣ ኢንስፔክሽን፣ኳራንቲንና ሬጉላቶሪ ዘርፍ    0

የግብርና ምርት ጥራት፣ ኃይጅንና ደህንነት ማስጠበቅ የጋራ ኃላፊነት ነው፡፡

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም (አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ)


በ2018 በጀት ዓመት በባለፉት 9 ወራት ጥራቱ፣ ኃይጅኑና ደህንነቱ የተጠበቀ የግብርና ምርትና ግብዓት ለተጠቃሚዎች ተደራሽ እንዲሆን የተጠናከረ የድጋፍና ክትትል እንዲሁም የቁጥጥር ሥራዎች ተሰርተዋል፡፡
በ9 ወራት ሥራ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ እንደተቀመጠው 2,353 ልኳንዳ ቤቶች ላይ 3 ጊዜ ቁጥጥር ለማድረግ ታቅዶ 3 ጊዜ ቁጥጥር በማድረግ ጥራትና ደህንነቱ የተረጋገጠ የሥጋ ምርት ለማህበረሰቡ እንዲቀርብ ተደርጓል፡፡
በሌላ በኩል ህገ-ወጥ የእንስሳት እርድ እና የሥጋ ዝውውር ለመከላከል 128 ቦታዎች ተለይተው ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ከእቅድ በላይ ሌሎች ያልተለዮትንም ተደራሽ በማድረግ 179 (>100%) ቦታዎች ላይ አስተማሪ እርምጃ መውሰድ ተችሏል፡፡
በተደረገው ድጋፍና ክትትል እንዲሁም በቁጥጥር ሥራ የተገኙ ግኝቶችም ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር የጋራ ተደርጎ ግብረ-መልስ ተሰቶበታል፡፡ ለቀጣይም የበለጠ አጠናክሮ ለመስራት የጋራ መግባባት ተፈጥሯል፡፡
የድጋፍና ክትትል ግምገማ መድረኩ ተሳታፊ የነበሩ ባለድርሻ አካላትና ግብዓት አቅራቢ ድርጅቶችም በጋራ በመስራታቸው ተገኘውን ውጤት አድንቀው በቀጣይ በግላቸው የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን የገለፁ መሆኑን የሰርተፊኬሽን፣ ኢንስፔክሽን፣ ካራንቲን እና ሬጉላቶሪ ዘርፍ ኃላፊ ም/ኮሚሽነር ፀጋ ለማ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments