የግብርና ምርት፣ ግብዓትና አገልግሎት መስጫ ተቋማት በስታንዳርድ መሰረት ህጋዊ ሆነው እንዲሰሩ ማድረግ ተችሏል፡፡
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም (አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ)
ለውጡን መሰረት አድርጎ የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን መቋቋሙና በማዕከል በዘርፍ ደረጃ የሰርተፊኬሽን፣ ኢንስፔክሽን፣ ካራንቲንና ሬጉላቶሪ ዘርፍ መፈጠሩ ቀደም ብሎ ከ2010 ዓ.ም በፊት የነበሩ ክፍተቶችን በማረም የግብርና ምርት፣ ግብዓትና አገልግሎት መስጫ ተቋማት በስታንዳርድ መሰረት ህጋዊ ሆነው እንዲሰሩ ማድረግ ተችሏል፡፡
የግብርና ምርት፣ ግብዓትና አገልግሎት ጥራት፣ ኃይጅንና ደህንነት ለማስጠበቅና አገልግሎቱ በስታንዳርድ እንዲሰጥ ለማድረግ ደንቦችና መመሪያዎች ተዘጋጅተው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የጋራ በማድረግ ተግባራዊ እየተደረጉ ይገኛል፡፡
በ2018 በጀት ዓመት በባለፉት 9 ወራት ለ31 የአትክልት ዘር ችርቻሮ ንግድ ድርጅቶች፣ ለ156 የፀረ-ተባይ መድኃኒቶች ችርቻሮ ንግድ ድርጅቶች እና ለ10 የፀረ-ተባይ መከላከል ርጭት አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች የብቃት ማረጋገጫ እንዲይዙ ተደርጓል።
ስታንዳርድ ከማስጠበቅ አንፃርም በግብርና ዘርፍ የብቃት ማረጋገጫ በወሰዱ 2,172 ድርጅቶች ላይ ክትትልና ቁጥጥር 3 ጊዜ ለማድረግ ታቅዶ ለ2,172 ድርጅቶች በዕቅዱ መሰረት 3 ጊዜ /100%/ ክተትልና ቁጥጥር ማድረግ መቻሉን የዘርፉ የ9 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ያሳያል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments