በተገልጋዮቻችን የነቃ ተሳትፎ የአርሶ አደርና የከተማ ግብርና ልማት ራዕይና ተልዕኮ እውን ይሆናል!፡፡
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 15 ቀን 2018 ዓ.ም (አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ)
የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የግብርና ቤተሰቦች በተለይም ቁልፍ ባለጉዳዮቻችን አርሶ አደሮች በሚያደርጉት የነቃ ተሳትፎ የአርሶ አደር እና የከተማ ግብርና ልማት ራዕይና ተልዕኮ እውን ይሆናል፡፡
ከተማ አስተዳደሩ አርሶ አደሮች ከከተማዋ ልማት ጋር አብረው እንዲለሙ ስትራቴጅ ነድፎ እየሰራ ይገኛል፡፡ በመሆኑም የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ተቋቁሞ ከማዕከል እስከ ወረዳ መዋቅር ኖሮት አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡
ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ ተገልጋዮች ተቋሙ የእኔ ነው በሚል ከግል ጉዳያቸው ባለፈ ለተቋሙ ራዕይና ተልዕኮ መሳካት የሚጠበቅባቸውን ሁሉ እያደረጉ እንደሚገኝ፤ ለዚህም አርሶ አደሮች እያደረጉት ያለው ሁለንተናዊ የነቃ ተሳትፎ ለአብነት የሚጠቀስ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
“ከሸማችነት ወደ አምራችነት” የሚለውን መርህ ይዘው አርሶ አደሮች ምርታቸውን በተለይም በሰንበት ገበያዎች ላይ በቀጥታ ለሸማቹ ማህበረሰብ እያቀረቡ ገበያ ከማረጋጋት ባለፈ እየተጫዎቱ ያለው ከተማዊ ኢኮኖሚያዊ ሚና ቀላል አለመሆኑንም ዋና ኮሚሽነር ባዮ ሽጉጤ አያይዘው ገልፀዋል፡፡
አርሶ አደሮችም መንግስት እያደረገላቸው ላለው ድጋፍ ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፤ ከግል ጉዳያቸው ባለፈም የኮሚሽኑ ራዕይና ተልዕኮ እንዲሳካ የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ለማድረግ ቃል ገብተዋል፡፡
ኮሚሽኑም የራሱ ቢሮ ኖሮት የተቀረፀውን ራዕይና ተልዕኮ እንዲወጣ ለማድረግ የአንበሳውን ድርሻ እንደሚወስዱ አንስተዋል፡፡
ም/ኮሚሽነር ወ/ሮ ሎኮ ዳለቻ እንደገለፁት እስካሁንም ቢሆን ለተመዘገበው ውጤት በተለይም ከ1.2 ሚሊዮን በላይ የከተማ ግብርና ተሳታፊና ተጠቃሚ አለ ሲባል የአርሶ አደሮች ሚና ቀላል የማይባል መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በሌላ በኩል የአርሶ አደሮችን ተሳትፎ ስንመለከት ከምርት አቅርቦት ጋር በተያያዘም ቢሆን በቀን ከ419,023 ሊትር በላይ ወተት እና በቁጥር ከ4,038,111 በላይ እንቁላል ለገበያ እንዲቀርብ የድርሻቸውን ሚና ተጫውተዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments