በባለፉት 7 ዓመታት በርካታ የከተማችን ዜጎች የ...

image description
- In አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን    0

በባለፉት 7 ዓመታት በርካታ የከተማችን ዜጎች የሥራ ዕድል ተፈጥሮላቸዋል፡፡

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 15 ቀን 2018 ዓ.ም (አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ)


በ2018 በጀት ዓመት በባለፈው 9 ወራት ብቻ በእንስሳት ሃብት ልማት ዘርፍ ለ19,893 ዜጎች የሥራ ዕድል መፈጠሩን የእንስሳት ሃብት ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ደጀኔ ጌታቸው ገልፀዋል፡፡ ይህ እንደማሳይ ይነሳ እንጂ በባለፉት 7 ዓመታት በርካታ የከተማችን ዜጎች የሥራ ዕድል ተፈጥሮላቸዋል፡፡


ዳይሬክተሩ አያይዘውም አዲስ የቤተሰብ ፍጆታ በከተማ ግብርና ተሳታፊና ተጠቃሚ ከማድረግ አንፃር በ9 ወር ሥራ አፈፃፀም በእንስሳት ሃብት ልማት 74,763 ታቅዶ 112,452 />100%/ መፈፀም ተችሏል ብለዋል፡፡


ሌላው ነባር በእንስሳት ሃብት ልማት ዘርፍ የተሰማሩ ተጠቃሚዎችን 334,026 ማስቀጠል የተቻለ ሲሆን ይህ አፈጻጸም በ2017 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት (191,696) ጋር ሲነጻጸር የ74% ብልጫን ያሳያል።


እንደ ዳይሬክተሩ ገለፃ ይህ ውጤት የተመዘገበበት በዋናነት ከማዕከል እስከ ተጠቃሚ ክፍተትን መሰረት ያደረገ የአቅም ግንባታ ሥራ በመስራት፣ ቴክኖሎጂና ግብዓትን በአግባቡ በመጠቀም፣ ተከታታይነት ያለው ሙያዊና ቴክኒካል ድጋፍ በማድረግ መሆኑን አንስተዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments