ለወተት ሃብት ፕሮጀክቱ ተጨማሪ ጊደሮች ወደ ማዕ...

image description
- In የእንስሳት ልማት ልህቀት ማዕከል    0

ለወተት ሃብት ፕሮጀክቱ ተጨማሪ ጊደሮች ወደ ማዕከሉ ገብተዋል።

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 18 ቀን 2018 ዓ.ም (አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ)


በእንስሳት ልማት እና ልህቀት ማዕከል  በማዕከሉ የወተት ሃብትን ለማሻሻል ተዘጋጅቶ ወደ ሥራ ለገባው የወተት ሃብት ልማት ፕሮጀክት የሚሆኑ ተጨማሪ ጊደሮች ወደ ማዕከሉ ገብተዋል።


ማዕከሉ የወተት ምርት እና ምርታማነት ለማሻሻል ለሚተገብረው ፕሮጀክት ከአሁን በፊት 9/ ዘጠኝ/ ጊደሮች ገብተው ወደ ሥራ የተገባ ሲሆን በዛሬው ዕለትም 3/ሦስት/ ተጨማሪ ጊደሮችን ማስገባት ተችሏል።


በዚህ ፕሮጀክት የሚከናወኑ ተግባራት የወተት ልማትን ከማሻሻል ባሻገር ለዝርያ ማሻሻል ስራው ወሳኝ እንደሚሆኑ ይጠበቃል። በእርባታ ሥራ ላይ ከተሰማሩት ማህበራት ውጭ ዝርያን ለማሻሻል በማዕከሉ እስካሁን በድምሩ 12 ጊደሮች ገቢ ሆነዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments