የከተማ ግብርና ባህል እየሆነ መጥቷል፡፡

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

የከተማ ግብርና ባህል እየሆነ መጥቷል፡፡

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 19 ቀን 2018 ዓ.ም (አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ)


የኮሚሽኑ ባለሙያዎች የከተማ ግብርና ሥራዎች በእንስሳት እና በእጽዋት ያሉበት ደረጃ በ9 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ምን እንደሚመስል በአካል ቤት ለቤት በመንቀሳቀስ በኦዲት የማረጋገጥ ሥራ አድርገዋል፡፡

በተደረገውም የኦዲት ሥራ የሌማት ትሩፋት ፕሮግራም፣ የፕሮጀክቶች አፈፃፀም፣ የእንስሳት እና እጽዋት ሃብት ልማት ውጤታማነት በተለይም በዶሮ እርባታ በፋሚሊ ቢዝነስ ወደ ሥራ የገቡ ተጠቃሚዎች ያሉበት ደረጃን አስመልክቶ ምርትና ምርታማነትን ውጤታማ ለማድረግ እየተሰራ ያለው ሥራ ታይቷል፡፡

የኦዲት ቡድኑም በነበረው የቤት ለቤት የኢንስፔክሽን ሥራ ከኦዲት ባለፈ ሙያዊ እና ቴክኒካል ድጋፍ አድርጓል፡፡

የኦዲት ቡድኑ ባደረገው የቤት ለቤት ምልከታ ከተማ ግብርና በከተማዋ ነዋሪዎች ዘንድ ባህል እየሆነ መምጣቱን አረጋግጧል፡፡ ይህ ደግሞ ማህበረሰቡ “ከሸማችነት ወደ አምራችነት” መሸጋገሩን ያመለክታል፡፡

በሌላ በኩል አዲስ አበባ ላይ ከተማ ግብርናን ተግባራዊ ማድረግ አይቻለም የሚለው አስተሳሰብ ተቀይሮ ዛሬ ከተማዋ በርካታ የግብርና ምርቶችን በራሷ አቅም ለመሸፈን ጥረት እያደረገች እና ከፍተኛ ውጤትም እየተመዘገበ መሆኑን ማሳያ ነው፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments