ትርጉም ያለው የቅንጅታዊ እና የባለድርሻ አካላት...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

ትርጉም ያለው የቅንጅታዊ እና የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ለውጤታማ ግብርና፡፡

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 21 ቀን 2018 ዓ.ም (አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ)


ከቅንጅታዊ እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ቅንጅት በመፍጠር የከተማ ግብርና ሥራዎችን የሚመለከቱ ጉዳዮች በትኩረት እየተሰራባቸው መሆኑን ማረጋገጥ፣ ሰፋፊ የከተማ ግብርና ኢንቨስትመንት አማራጮችንና እምቅ አቅሞችን መለየትና መጠቀም፣ የከተማ ግብርና ሥራዎች የሚስፋፉበትን እና የሚጠናከሩበትን ስልት መቀየስ እንዲሁም በዘርፉ ለተሰማሩ ተጠቃሚዎች የሚያስፈልጋቸውን ቴክኖሎጂና ግብዓት፣ ሙያዊ እና ቴክኒካል ድጋፍ እንዲያገኙ በማድረግ ውጤታማነታቸውን ማረጋገጥ የኮሚሽኑ ዋንኞቹ ተግባራት ናቸው፡፡ 


ለነዚህ ተግባራት ውጤታማነት ኮሚሽኑ በ2018 በጀት ዓመት 9ወራት ውስጥ ከሚመለከታቸው ቁልፍ ቅንጅታዊ እና ባለድርሻ አካላት ጋር በእጽዋት ሃብት ልማት ዘርፍ የሰራቸውን ስራዎች መነሻ አድርጎ ፓናል ውይይት አድርጓል፡፡ በፓናል ውይይቱም ጠንካራ ጎኖች እና ውስንነቶች ተነስተው የጋራ ተደርገዋል፡፡


ኮሚሽኑ፣ ቅንጅታዊ ተቋማት እና ቁልፍ ባለድርሻ አካላት በጋራ ተቀራርበው መስራት እንደሚገባቸው፣ የተሰሩ ሥራዎችን በወቅቱ መገምገም እንዳለባቸው፣ ለቴክኖሎጂና ለዕውቀት ሽግግር ስልት መንደፍ እንደሚጠበቅባቸው፣ በየዘርፉ ልምድ ልውውጥ እንደሚያስፈልግ በውይይቱ ተነስቶ የቀጣይ ዕቅድ አካል ሆኖ ከእስካሁኑ በእጥፍ እንዲተገበር አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡-
YouTube ➲ https://bit.ly/4hnxoMs
Telegram ➲ https://bit.ly/4h2cPVT
 Facebook ➲ https://bit.ly/4gjsu1M
Tiktok ➲ https://bit.ly/4gdXK2o
ከላይ በተገለጹት አድራሻዎቻችን ይከታተሉን፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments