የእንስሳትን ጤና መጠበቅ የሚፈለገውን ምርት ለማ...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

የእንስሳትን ጤና መጠበቅ የሚፈለገውን ምርት ለማግኘት ቀደሚው ተግባር ነው፡፡

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 21 ቀን 2018 ዓ.ም (አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ)


የተጠናከረ የእንስሳት ጤና ላቦራቶሪ ምርመራ እና ቅድመ መከላከል ምርትና ምርታማነት ላይ እንዲሁም የምርት ጥራትና ደህንነትን ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና አለው፡፡


የእንስሳት ጤና ላቦራቶሪ ቡድን መሪ አቶ ፍስሃ ክንፈ ከሰጡን መረጃ አንፃር በባለፉት ሦስት ዓመታት የተሰሩ ሥራዎችን እንደ ናሙና ወስደን ብናይ በፓራሳይቶሎጂ (የውስጥ ጥገኛ) 3,500 ናሙናዎች ከወተት ላም አዛባ እና 1,500 ናሙናዎች ከዶሮ ኩስ በመውሰድ ምርመራ ተደርጓል፡፡


ሌላው በማይክሮባዮሎጂ ወደ 12,000 የሚሆኑ የወተት፣ የደም እና የደም ቅራሪ ናሙናዎች ተወስደው ምርመራ ተደርጓል፡፡ በሴሮ-ኢሚንዮሎጂም ወደ 600 የሚሆን የደም ቅራሪ ናሙናዎች ምርመራ ተደርጓል፡፡


የእንስሳት ጤና ላቦራቶሪ ቡድን መሪ አቶ ፍስሃ ክንፈ እንደገለፁልን የተገኘው የምርመራ ውጤት የእንስሳት ሃኪሞችን አቅም አሳድጓል፣ ጠንካራ ድጋፍና ክትትል ለማድረግ አግዟል፣ የእንስሳት ተዋፅኦ ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር አድርጓል፣ ከእንስሳት ወደ ሰው ሊተላለፉ የሚችሉ በሽታዎችን ቀድሞ ለመከላከል አግዟል፣ የዶሮ በሽታን በቀላሉ ቀድሞ ለመከላከል እንዲቻል ትልቅ ሚና ተጫውቷል ብለዋል፡፡


ለበለጠ መረጃ፡-
YouTube ➲ https://bit.ly/4hnxoMs
Telegram ➲ https://bit.ly/4h2cPVT
 Facebook ➲ https://bit.ly/4gjsu1M
Tiktok ➲ https://bit.ly/4gdXK2o
ከላይ በተገለጹት አድራሻዎቻችን ይከታተሉን፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments