በከተማ ግብርና የተሰሩ ሥራዎች ከፍተኛ ውጤት የ...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

በከተማ ግብርና የተሰሩ ሥራዎች ከፍተኛ ውጤት የተመዘገበባቸው መሆኑን የአገልግሎት አሰጣጥ መማክርት ጉባኤ ገለፀ፡፡

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 23 ቀን 2018 ዓ.ም (አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን)


የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የአገልግሎት አሰጣጥ መማክርት ጉባኤ ባለፉት 9 ወራት ውስጥ የተሰራውን የኮሚሽኑን ዕቅድ አፈፃፀም በመገምገም በመስክ የተሰሩ ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን (የዶሮ እርባታ፣ የወተት ላም እርባታ፣ ማድለብ፣ የአሳማ እርባታ፣ የአሳ እርባታ፣ የመኖ ማቀነባበር፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት እና የሃይድሮ ፎኒክ ቴክኖሎጂ) ተዘዋውሮ ተመልክቷል፡፡


የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር እና የመማክርት ጉባኤው ም/ሰብሳቢ አቶ ባዮ ሽጉጤ የመማክርት ጉባኤው የኮሚሽኑን የአገልግሎት አሰጣጥ ፍትሐዊነት የምናረጋግጥበት፣ የተገልጋዮችን ተጠቃሚነትና እርካታ የምናሳድግበት ቁልፍ መሳሪያ መሆኑን ገልፀዋል፡፡


የመማክርት ጉባኤው ዋና ሰብሳቢ አቶ አስራት ገመቹ በበኩላቸው ኮሚሽኑ የአርሶ አደሮችንም ሆነ የከተማ ግብርና ተጠቃሚዎችን በፍትሐዊነት በማገልገል ሰው ላይ ያረፈ ውጤት አስመዝግቧል ብለዋል፡፡ አያይዘውም በተለይ አርሶ አደሮች ከከተማዋ ልማት ጋር አብረው እንዲለሙ እየሰራ ያለው ሥራ እጅግ የሚያስመሰግነው መሆኑን ገልፀዋል፡፡


የመማክርት ጉባኤው አባላት በመስክ ተዘዋውረው የተመለከቱት የከተማ ግብርና ሥራ አዲስ አበባ ከተማ በምግብ ራሷን ለመቻል እየሰራች ለመሆኑ ትልቅ ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል፡፡


አያይዘውም በኮሚሽኑ በኩል እየተሰራ ያለው ሥራ እና ለውጡ ይዞት የመጣው መልካም ነገር በከተማ አስተዳደሩ ሥር ያለው አርሶ አደር በመብቱ ተጠቃሚ የሚሆንበትን እና ከከተማዋ ልማት ጋር አብሮ የሚለማበትን ዕድል ፈጥሯል ብለዋል፡፡


ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ መንግስት ለከተማ ግብርና መስፋፋትና መጠናከር እንዲሁም ለአርሶ አደሩ ከከተማዋ ልማት ጋር አብሮ መልማትና መበልፀግ ልዩ ትኩረት በመስጠት 7/24 በመስራት አሁን ያለው ውጤት ተመዝግቧል፤ ነገር ግን የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥና በምግብ ራስን መቻል ለነገ የማይባል ሥራ በመሆኑ ልዩ ትኩረት በመስጠት በቴክኖሎጂ በመታገዝ ምርታችንን ማሳደግ ይገባል ብለዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments