ህገ-ወጥ የእንስሳት እርድ እና ሥጋ ዝውውር ህብረተሰቡን ለተላላፊ በሽታዎች ተጋላጭ ያደርገዋል፡፡
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 24 ቀን 2018 ዓ.ም (አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን)
የሰርተፊኬሽን፣ ኢንስፔክሽን፣ ኳራንቲን እና ሬጉላቶሪ ዘርፍ በቄራዎች ጤንነቱ፣ ደህንነቱ እና ኃይጅኑ የተጠበቀ የሥጋ ምርት ለማህበረሰቡ እንዲደርስ እየተደረገ ያለበትን ሁኔታ የማዕከልና የክፍለ ከተማ ቡድን መሪዎችን አስተባብሮ ምልከታ አድርጓል፡፡
ህገ-ወጥ የእንስሳት እርድ እና ሥጋ ዝውውርን ለመቆጣጠር በግብረ-ኃይል ከሚሰራው ሥራ ጎን ለጎን ቄራዎች አቅማቸውን በማሳደግ አገልግሎቱን በስታንዳርድ መስጠት ይጠበቅባቸዋል፡፡
ኮሚሽኑ ካስመዘገባቸው ውጤቶች መካከል አንዱ ጥራቱ፣ ደህንነቱና ኃይጅኑ የተጠበቀ የሥጋ ምርት ለማህበረሰቡ እንዲደርስ ቄራዎች ከቅድመ-እርድ እስከ ልኳንዳ ቤት አገልግሎቱ በስታንዳርድ እንዲተገበር አሰራር የተዘረጋ መሆኑ ነው፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments