በ104 ማኅበር የተደራጁ 540 አርሶ አደሮች በእንስሳት ልማት እና ልህቀት ማዕከል ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ
አርሶ አደሮች ከከተማው ልማት ጋር አብረው እንዲለሙ ከማድረግ አንፃር ከለውጥ በኋላ በልማት ምክንያት ይዞታቸውን የለቀቁ የልማት ተነሺ አርሶ አደሮች በተለያዮ የሥራ ዘርፎች ላይ እንዲሰማሩ በማድረግ ዘርፈ ብዙ መልሶ የማቋቋምና የማልማት ሥራ ተሰርጧል፡፡
ከነዚህ የልማት ሥራዎች መካከል አንዱ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 በ14 ሄክታር መሬት ላይ የተገነባው የእንስሳት ልማት እና ልህቀት ማዕከል ሲሆን የወተት፣ የከብት ማደለቢያ፣ የዶሮ እርባታ፣ የመኖ ማቀነባበሪያና 32 ሱቆችን በማሟላት 104 ማኅበራትንና 540 አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments